በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ አለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል

በተለያዩ አገራት በቅዳሜና እሁድ በተካሄዱ የማራቶን፣ የግማሽ ማራቶንና የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተለያዩ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።
በፖርቹጋል በተካሄደው የሊዝበን ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው በመግባት አሸንፈዋል።
በሴቶቹ አትሌት መስከረም ማሞ ርቀቱን 2:28:04 በመጨረስ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ ጠጅቱ ስዩም ደግሞ በ7 ማይክሮ ሰከንድ ዘግይታ ሁለተኛ ሆናለች።
በሻንቄ ቢሎ 2:28:15 በማስመዝገብ ሦስተኛ ወጥተዋል። ስንታየሁ ጥላሁን 2:28:19 በመሮጥ አራተኛ፣ አበበች አፈወርቅ 2:29:00 በማስመዝገብ አምስተኛ ሆነዋል።
ዋጋነሽ አሰጌ 2:33:00 ስምንተኛ፣ ገነት ሳህሌ 2:34:04 9ኛ ወጥተዋል።

በወንዶች ዘርፍ ደሳለኝ ይሌ 2:09:08 በሆነ ጊዜ አራተኛ ሲወጣ፣ ደምሱ ገመዳ 2:11:29 ስምንተኛ፣ ደቻሳ ኑጉሳ 2:12:53 አሥረኛ እና ደረበ ረጋሳ 2:20:21 አሥራ ሁለተኛ ሆነዋል።
በኦስትሪያ ብሬገንዝ ማራቶን ፍቅሬ በቀለ 2:08:49 በመሮጥ አሸንፏል።
በጀርመን ሙኒክ አላዛር ተፈራ 2:10:53 በሆነ ጊዜ አንደኛ ሲወጣ ገብሬ መልሴ 2:24:49 በመሮጥ ሦስተኛ ወጥቷል።
በካናዳ ሞንትሪያል ማራቶን አለም ገብረማርያም 2:29:17 በመሮጥ የሴቶችን ውድድር አሸንፋለች።
በወንዶች ሃይሌ ኪንዲያ ተስፋዬ 2:16:48 በማስመዝገብ ሁለተኛ ወጥቷል።

በሮማኒያ ቡካሬስት ማራቶን ተሾመ ዳባ ቡሌሳ 2:23:32 በመሮጥ አራተኛ ሆኗል።
በፖርቱጋል ሊዝበን ግማሽ ማራቶን በወንዶች ዘርፍ ዘሪሁን አዱኛ 1:02:01 በሆነ ሰዓት አሸንፏል።
አትሌት አቤል በቀለ 1:02:09 በመሮጥ አራተኛ፣ ፀጋዬ አያሌው 1:02:21 አምስተኛ፣ ለታ አበበ 1:05:04 አሥረኛ ወጥተዋል።

በሴቶች ኩፍቱ ጣሂር ዳዲሶ 1:09:04 በማስመዝገብ ሦስተኛ ስትወጣ፣ ደባሽ ከላሊ 1:09:25 አራተኛ፣ ፈንታዬ አዳነ 1:09:48 አምስተኛ ሆነዋል።
መገርቱ ሚደቅሳ 1:12:21 ሰባተኛ፣ አስቻለ ሽቱ 1:13:52 ስምንተኛ ወጥተዋል።
ጀርመን ግሬት 10ኬ፣ በርሊን በወንዶች ውድድር ከፍያለው ክፍሌ 28:15 በሆነ ጊዜ በመሮጥ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በሴቶች ብርቱካን ሞላ 30:50 በማስመዝገብ ሁለተኛ ወጥታለች።
