ዊሊያም ሳሊባ ወደ ልምምድ ተመለሰ፤ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ፒዬሮ ኢንካፒዬ  የጉዳታቸው ሁኔታ ታወቀ

0
IMG_20261013_123156_820

ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ፒዬሮ ኢንካፒዬ በአንድ ቀን የቁርጭምጭሚት ጉዳት ማስተናገዳቸው ለአርሰናል እና ለሚኬል አርቴታ እጅግ በጣም አጋጣሚና መጥፎ ዜና ነው! ጨዋታ ላልተጫወቱ ወይም ጥቂት ደቂቃ ላገኙ ተጫዋቾች በተዘጋጀ የማገገሚያ ልምምድ (warm-down) ላይ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ፒዬሮ ኢንካፒዬ በአንድ ቀን የቁርጭምጭሚት ጉዳት ማስተናገዳቸው እውነትም ያልታደለ ያደርገዋል።

አርቴታ በሰጠው  ጋዜጣዊ መግለጫ የተጨዋቾቹን  መጎዳት በእሱ ላይ የነጣጠረ በመሆኑ እሱ ግን መከላከል መርጧል። “ተጫዋቾች ጨዋታ እንዲያገኙ ልምምድ ካላደረጉ ሜዳ ሲገቡ ፍጥነትና ተፅዕኖ አይኖራቸውም”  ካለ በኋላ። ጉዳቱን አስቀድሞ ለማወቅ “የክሪስታል ኳስ (crystal ball) ቢኖረኝ ኖሮ ሁላችሁም ጃኩዚ ውስጥ ግቡ እላቸው ነበር” በማለት በዕድል ማጣት የመጣ መሆኑን ገልጿል።

ሁለቱም ለምርመራ (Scan) ቢሄዱም የፒዬሮ ኢንካፒዬ ጉዳት ከዙቢሜንዲ ይልቅ ጠንከር ያለና አሳሳቢ እንደሆነ ተነግሯል። እንዲያውም ከልምምድ ሜዳው በሊድሱ ግብ ጠባቂ ኢላን መሊዬ ተሸክሞት ሲወጣ መታየቱ ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል።

ቡድኑ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሊል ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የተጫዋቾች ጥልቀት (Squad depth) ላይ ትልቅ ራስ ምታት ይፈጥርበታል። በተለይ በፈረንሳይ ሊግ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ሊልን ለመግጠም የነዚህ ተጫዋቾች አለመኖር የአርቴታን እቅድ ያዛባል።

ይሁንና ለጋነሮቹ መልካም ዜና የሆነው ዊሊያም ሳሊባ ለብቻው ልምምድ መጀመሩ ነው።

በቅርብ ሰዓታት ውስጥ ከለንደን በወጡ መረጃዎች መሠረት የሁለቱ ተጫዋቾች የጉዳት ጊዜ ሰሌዳ (Return timeline) መለየት ተጀምሯል።

ማርቲን ዙቢሜንዲ፡ የቁርጭምጭሚት መጋጨት (Knock) የገጠመው ሲሆን፣ የጉዳቱ መጠን ቀሊል በመሆኑ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ይጠበቃል።

ፒዬሮ ኢንካፒዬ፡ እሱ ላይ የደረሰው የቁርጭምጭሚት መጣመም (Sprained ankle) ግን ከባድ በመሆኑ ቢያንስ ለሦስት ሳምንታት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ታውቋል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከሊል ጋር ለሚደረገው ጨዋታ አርቴታ በግራ መስመር ተከላካይነት ላይ በኢንካፒዬ ምትክ ሪካርዶ ካላፊዮሪን በቋሚነት የመጠቀም ዕድሉ ሰፊ ነው። በሌላ በኩል፣ ፈረንሳዊው ሊል በአዲሱ አሰልጣኙ ዴቪድ አንቸሎቲ (የካርሎ አንቸሎቲ ልጅ) እየተመራ በሊግ 1 ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ጠንካራ ቡድን በመሆኑ ጨዋታው ለአርሰናል ቀላል አይሆንም

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail