በሊዩብሊያና ማራቶን አትሌት ሀብታምነሽ ተስፋይ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታምነሽ ተስፋይ በስሎቬኒያ ሊዩብሊያና ማራቶን የሴቶች ውድድርን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
አትሌቷ በ2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ውድድር ረዳት ኢንስፔክተር ትግስት ገዛኸኝ 2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በሌላ ዜና በኒው ዴሊ ግማሽ ማራቶን አትሌት ውድነሽ ዓለሙ አሸንፋለች ።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ውድነሽ ዓለሙ በሕንድ ኒው ዴሊ በተካሄደው የቬዳንታ ዴሊ ግማሽ ማራቶን የሴቶች ውድድርን አሸንፋለች።
አትሌቷ ርቀቱን በ1 ሰዓት 6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በማጠናቀቅ የድል ባለቤት ሆናለች።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያስመዘግቡት ድል ቀጥሏል::
