በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጁ

0
IMG_20261020_084944_570

የ2026 አምስተርዳም ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችና በሴቶች ምድብ አሸናፊ በመሆን ድንቅ የሆነ ውጤት አስመዝግበዋል።

በወንዶች ምድብ አትሌት ለሚ ብርሃኑ የማራቶን ርቀቱን በ2:03:33 በማጠናቀቅ የግል ምርጥ ሰዓቱን (Personal Best) አሻሽሎ የውድድሩን አሸንፏል ።

በዚሁ ምድብ ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ 10ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።

ከ2ኛ እስከ 8ኛ ያሉትን ደረጃዎች ደግሞ ኬንያውያን አትሌቶች ይዘዋል።

በሴቶች ምድብ አትሌት ቡዜ ድሪባ በአንደኝነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ሌላ የድል ዜና አብስራለች።

አትሌቷ የማራቶን ርቀቱን በ2:16:10 በማጠናቀቅ የውድድሩን አሸንፋለች ።

አትሌት አይናለም ደስታ 2ኛ ፣አትሌት መሰረት በለጠ 3ኛ፣አትሌት ትርንጎ ሙሉ 4ኛ፣አትሌት መስታወት ፍቅር 5ኛ እና አትሌት ግርማዊት ገብረዝሄር 6ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በዚህም የ2026 አምስተርዳም ማራቶን በሁለቱም ፆታ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድሮች ያላትን የበላይነት ማስቀጠሏን አረጋግጣለች።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail