አትሌት ታምራት ቶላ እና አትሌት አንቺንአሉ ደሴ የቤጂንግ ማራቶንን አሸነፉ

0
IMG_20261020_084956_745

ተጠባቂው የቤጂንግ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተጠናቋል።

በወንዶች ምድብ የኦሊምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮኑ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶንን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ተቀዳጅቷል።

አትሌት ታምራት ቶላ 2:03:10 በሆነ ጊዜ ውድድሩን በማጠናቀቅ የውድድሩን የወንዶች ክብረወሰን ማሻሻል ችሏል።

ከ2019 ጀምሮ በኬንያዊው አትሌት ማቲው ኪሶሪዮ የተያዘውን 2:07:06 የውድድር ክብረወሰን በ3 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በማሻሻል አዲስ ታሪክ ሰርቷል።

ይህ ውጤት በቻይና ከተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች መካከል ፈጣን ከሆኑ ሰዓቶች አንዱ ነው።

በዚሁ ምድብ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሙክታር እድሪስ 2:04:34 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሲወጣ፣ አትሌት አዳነ ከበደ 2:05:10 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።

በሴቶች ምድብ አንቺንአሉ ደሴ ድሏን ደገመች

በሴቶች ምድብ ጀግናዋ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ የቤጂንግ ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ ድሏን ደግማለች።

አትሌት አንቺንአሉ 2:20:36 በሆነ ጊዜ ውድድሩን በማጠናቀቅ አንደኛ ወጥታለች።

አትሌቷ በ2025 የቤጂንግ ማራቶንን ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮም ድሏን በመድገም በውድድሩ ላይ ያላትን ብቃት አረጋግጣለች።

ኢትዮጵያ በቤጂንግ ማራቶን ያስመዘገበችው ይህ ድል የአገራችንን የማራቶን ብቃትና የአትሌቲክስ የበላይነት የሚያሳይ ነው።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail