የዓለም አትሌቲክስ ማህበርየዋንዳ ዳይመንድ ሊግና (Wanda Diamond League) የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና መግለጫ ሰጠ

በኢሜል የዓለም አትሌቲክስ ማህበር በላከልን የፕሬስ ሪሊስ በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ የአትሌቲክስ ውድድሮች አንዱ ወደሆነው ወደ የዋንዳ ዳይመንድ ሊግና (Wanda Diamond League) የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በተመለከተ የላከልንን እናቅርብ።
የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ውድድር በአንድ ቀን ውስጥ ተጀምረው የሚያልቁ የዓለማችን ምርጥ የትራክና ሜዳ (Track and Field) ውድድሮች ስብስብ ሲሆን፣ የዓለምን ኮከብ አትሌቶች በአንድ ላይ የሚያገናኝ ታላቅ መድረክ ነው።
የውድድር ጊዜ እና ቦታ
የመጀመሪያው ውድድር: ውድድሩ በሜይ 7, 2027 (ሚያዚያ 29, 2019 ዓ.ም.) በዶሃ፣ ኳታር ይጀምራል።
የመጨረሻው ፍጻሜ (Final): ውድድሩ በኦገስት 25-26, 2027 (ነሐሴ 19-20, 2019 ዓ.ም.) በዙሪክ፣ ስዊዘርላንድ በሚደረገው ታላቅ የፍጻሜ ውድድር ይጠናቀቃል።
በዓመቱ ውስጥ ውድድሩ በ4 አህጉራት፣ 15 ከተሞች እና በ14 ተከታታይ ስብሰባዎች (Meetings) ላይ ይካሄዳል።
የውድድሩ ስርዓት እና ይዘት
32 የውድድር ዘርፎች (Disciplines): አትሌቶች በ32 የተለያዩ የአትሌቲክስ ዘርፎች (በሩጫ፣ በዝላይ እና በውርወራ) ውስጥ ነጥብ ለመሰብሰብ ይወዳደራሉ።
እያንዳንዱ የውድድር ዘርፍ በዓመቱ ውስጥ ከ4 እስከ 8 ጊዜ ይስተናገዳል። አትሌቶች በእነዚህ ውድድሮች ላይ በሚያስመዘግቡት ውጤት ነጥብ እያከማቹ፣ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ብቻ ወደ ዙሪኩ የፍጻሜ ውድድር ያልፋሉ።
ይህ የ2027 የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ በሴፕቴምበር 2027 (መስከረም 2020 ዓ.ም.) በቤጂንግ፣ ቻይና ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና (World Athletics Championships) አትሌቶች ብቃታቸውን የሚፈትኑበት ወሳኝ መድረክ ይሆናል።
የዳይመንድ ሊግ በተለይ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች (በ5,000 ሜትር፣ 10,000 ሜትር እና በ3,000 ሜትር መሰናክል) የሜዳሊያ እና የክብር ምንጭ ነው።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዳይመንድ ሊግ ታሪክና ክብረ-ወሰኖች
የ2027 የቤጂንግ ዓለም ሻምፒዮና ውድድር
የ2027 የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ (Wanda Diamond League) የውድድር ዘመን ሙሉ የቀን መቁጠሪያ (Calendar) በይፋ የወጣ ሲሆን፣ አትሌቶች በ14 ከተሞች ነጥብ ለመሰብሰብ የሚያደርጉትን ፉክክር ተከትሎ ወደ ዙሪክ የፍጻሜ ውድድር የሚያመሩበትን ሙሉ ፕሮግራም በዝርዝር እንመልከት።
የ2027 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ሙሉ የውድድር ፕሮግራም
- ዶሃ (Doha) ኳታር 🇶🇦ሜይ 7, 2027
2 .ሻንጋይ/ከቺያዎ (Shanghai/Keqiao) ቻይና 🇨🇳ሜይ 15, 2027
3.ዚያሜን (Xiamen) ቻይና 🇨🇳ሜይ 22, 2027
4.ሮማ (Rome) ጣሊያን 🇮🇹ሜይ 27, 20275ራባት (Rabat) ሞሮኮ 🇲🇦ሜይ 30, 2027
6.ኦስሎ (Oslo) ኖርዌይ 🇳🇴ጁን 3, 20277 ስቶክሆልም (Stockholm)
7.ስዊድን 🇸🇪ጁን 6, 2027
8.ፓሪስ (Paris) ፈረንሳይ 🇫🇷ጁን 25, 2027
9.ዩጂን (Eugene) አሜሪካ 🇺🇸ጁላይ 3, 2027
10.ሞናኮ (Monaco) ሞናኮ 🇲🇨ጁላይ 9, 2027
11.ሎዛን (Lausanne) ስዊዘርላንድ 🇨🇭ጁላይ 13, 2027
12.ለንደን (London) ታላቋ ብሪታንያ 🇬🇧ጁላይ 17, 2027
13.ሲሌሲያ (Silesia) ፖላንድ 🇵🇱ኦገስት 15, 2027
14.ብራሰልስ (Brussels) ቤልጂየም 🇧🇪ኦገስት 20, 2027
15. 🏆ዙሪክ (Zurich Final) ስዊዘርላንድ 🇨🇭ኦገስት 25–26, 2027
የቤጂንግ 2027 የዓለም ሻምፒዮና አዲስ ማሻሻያ
ከዳይመንድ ሊጉ መዝጊያ ሁለት ሳምንት በኋላ በቤጂንግ፣ ቻይና የሚካሄደው 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና (World Athletics Championships) ላይ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር የአንድ ቀን የቀን ማሻሻያ ማድረጉ ታውቋል።
ውድድሩ መጀመሪያ ከሴፕቴምበር 11 እስከ 19 እንዲካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ከሴፕቴምበር 10 እስከ 19, 2027 እንዲካሄድ ተወስኗል። ይህ የተደረገበት ምክንያት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ (Opening Ceremony) በመጀመሪያው ቀን ከምሽቱ የውድድር መርሃ-ግብር ጋር አብሮ እንዲከናወንና አትሌቶች በሙሉ 10ሩም ቀናት በምሽት ክፍለ-ጊዜ (Evening Session) መወዳደር እንዲችሉ ለማድረግ ነው።
በተጨማሪም በ2027 የዳይመንድ ሊግ ማጠቃለያ የየዘርፋቸው አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ለቤጂንጉ የዓለም ሻምፒዮና ቀጥታ ማለፊያ “ዋይልድ ካርድ” (Wild Card) እንደሚያገኙ ተረጋግጧል።
