የአርቲስቲክ ጂምናስቲክ (ሮተርዳም) ውድድር እየተጠናቀቀ ነው

0
Screenshot_2026_1023_071032~2

በኢሜል የዓለም ጂምናስቲክ ፌዴሬሽን በላከልን የፕሬስ ሪሊስ በአርቲስቲክ እና ሪዝሚክ ጂምናስቲክ የአለም ሻምፒዮናዎች ለሎስ አንጀለስ 2028 (LA 2028) ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹን ተሳታፊ ሀገራት ማረጋገጣቸውን ታውቋል።

የተላከልን ኢሜል በሮተርዳም (ሆላንድ) እና በፍራንክፈርት (ጀርመን) በተደረጉት ውድድሮች ላይ የታዩ ታሪካዊ ስኬቶችን የያዘ ነው፣ አሸናፊዎቹ ሀገራት ቀድመው የኦሊምፒክ ትኬታቸውን ቆርጠዋል በማለትም ይገልጻል።

የአርቲስቲክ ጂምናስቲክ (ሮተርዳም)

በወንዶችም በሴቶችም የመጀመሪያዎቹን ሦስት ደረጃዎች የያዙት ሀገራት በቀጥታ ለአሜሪካው ላስቬገስ 2028 አልፈዋል።

በወንዶች ጃፓን (ወርቅ)፣ ሩሲያ (ብር) እና ቻይና (ነሐስ) ደረጃቸውን በማረጋገጥ የኦሊምፒክ ቦታቸውን አረጋግጠዋል።

በሴቶች ቻይና የ20 ዓመት የውጤት ጥማትን በመስበር ታሪካዊ የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፣ አሜሪካ በገዛ ሀገሯ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ በማግኘት ቦታዋን አረጋግጣለች። ጃፓን ደግሞ ከ1966 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የነሐስ ሜዳሊያ በመውሰድ ሦስተኛዋ ሀገር ሆናለች።

የሪዝሚክ ጂምናስቲክ (ፍራንክፈርት)

በነሐሴ ወር በተካሄደው የሪዝሚክ ጂምናስቲክ ውድድር በተናጠል (Individual) እና በቡድን (Group) የመጀመሪያዎቹን ሦስት ደረጃዎች በመያዝ ለኦሊምፒክ ያለፉት ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፦

የውድድር ዘርፍያለፉት ሀገራት

(የመጀመሪያዎቹ 3 ደረጃዎች)በተናጠል (Individual) ውድድር ጀርመን 🇩🇪 ፣ ቡልጋሪያ 🇧🇬 ፣ ጣሊያን 🇮🇹 ሲሆኑ ፤በቡድን (Group)ስፔን 🇪🇸 ፣ ጃፓን 🇯🇵 ፣ እና ብራዚል 🇧🇷 ናቸው፡፡

በኔዘርላንድስ ሮተርዳም አሆይ (Rotterdam Ahoy) አሬና ውስጥ እየተካሄደ ያለው 54ኛው የአርቲስቲክ ጂምናስቲክስ ዓለም ሻምፒዮና እጅግ አጓጊ ፉክክርና ትልቅ ድራማ ያስተናገደበት ነበር። የዚህ ውድድር የቡድን ፍጻሜዎች (Team Finals) የተከናወኑት በጥቅምት 20 እና 21 ነው።

የወንዶች ቡድን የፍጻሜ ውድድር (ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20)

የወንዶች ፍጻሜ የዓለም የጂምናስቲክ ኃያላን በሆኑት በጃፓንና በቻይና መካከል ከባድ ፍልሚያ የታየበት ነበር።

የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ሻምፒዮኖቹ ኦካ ሺኖሱኬ (Oka Shinnosuke) እና ሃሺሞቶ ዳይኪ (Hashimoto Daiki) የመሩት የጃፓን ቡድን በ251.928 አጠቃላይ ነጥብ የወርቅ ሜዳሊያውን በመውሰድ የዓለምነቱን ዘውድ አስጠብቋል።

በውድድሩ አጋማሽ ላይ የታላቋ ብሪታንያ ቡድን (በቫውልት/Vault ባሳዩት ድንቅ ብቃት) እና ቻይና መሪነቱን ይዘውት የነበረ ቢሆንም፣ በ5ኛው ዙር ብሪታንያ ባጋጠማት መውደቅ (Fall) ምክንያት ጃፓን ወደ መሪነት መጣች።

በፈታኙ የኮሪዞንታል ባር (Horizontal Bar) ውድድር ላይ የጃፓኑ ሃሺሞቶ ዳይኪ በራሱ ምርጫ መጨረሻ ላይ ወጥቶ እጅግ አስደናቂና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንቅስቃሴ በማሳየት 14.866 ነጥብ አስመዝግቦ የሀገሩን ወርቅ አረጋግጧል፡፡

የሴቶች ቡድን የፍጻሜ ውድድር (ረቡዕ፣ ጥቅምት 21)

የሴቶች ቡድን ፍጻሜ ደግሞ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ጥማት የተሰበረበት ነበር።

የቻይና የሴቶች ቡድን ለ20 ዓመታት ያህል የናፈቃትን የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ በሮተርዳም ማሳካት ችላለች።

ጠንካራዋ አሜሪካ የብር ሜዳሊያ ስታገኝ፣ ጃፓን ደግሞ ከ1966 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች ቡድን የነሐስ ሜዳሊያ በመውሰድ ታሪክ ሰርታለች።

ይህ የሮተርዳም ውድድር ለሀገራቱ ሜዳሊያ ብቻ ሳይሆን ለLA 2028 ኦሊምፒክ በቀጥታ የሚያሳልፍ የ5-ሰው ኮታ (Quota) ያስገኘ በመሆኑ ውጥረቱ እጅግ የበረታ ነበር።

የሮተርዳሙ ውድድር እስከ ጥቅምት 25 (ጥቅምት 15 በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ድረስ በተናጠል አጠቃላይ ብቃት (All-Around) እና በተለያዩ መሣሪያዎች (Apparatus Finals) ይቀጥላል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail