በተለያዩ አገራት በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጁ

0
IMG_20261027_123517_270

በጀርመንና በአየርላንድ በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችና በሴቶች ምድብ ድል በመቀዳጀት አስደናቂ ውጤት አስመዝግበዋል።


በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደው የ2026 ፍራንክፈርት ማራቶን በወንዶች ምድብ አትሌት ጂራታ ሌሊሳ 2:05:26 በሆነ ሰዓት የግል ምርጥ ስዓቱን በማስመዝገብ የውድድሩን ድል ተቀዳጅቷል። አትሌት አቤ ጋሻሁን ደግሞ 2:07:19 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 6ኛ ደረጃን ይዟል


በሴቶች ምድብ አትሌት ዘይነባ ይመር 2:19:45 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት በማጠናቀቅ ድል አስመዝግባለች።
በዚሁ ውድድር በሴቶች ምድብ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል።


አትሌት በሪሃ ገ/ዮሐንስ 2:22:46 በሆነ ሰዓት 3ኛ፣ አትሌት አሰለፍ አማረ 2:25:31 በሆነ ሰዓት 4ኛ፣ አትሌት ስራነሽ ይርጋ 2:26:05 በሆነ ሰዓት 5ኛ፣ አትሌት ምህረት ገመዳ 2:26:49 በሆነ ሰዓት 6ኛ፣ አትሌት ብርቄ በየነ ደግሞ 2:31:00 በሆነ ሰዓት 9ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሌላ ዜና በአየርላንድ በተካሄደው የደብሊን ማራቶንም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆነዋል።


በወንዶች ምድብ አትሌት አባይ አለሙ 2:10:29 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።
በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት ዘነቡ ፍቅዳው 2:24:26 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የውድድሩን ድል ተቀዳጅታለች።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail