የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ2019 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤና የስታዲዮም ግንባታ

0
FB_IMG_1793525649979

ጉባኤዉ ላይ የስፖርት ማህበሩ አባላት፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የስፖርት ማህበሩ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

‎በቅርቡ የማህበሩን ህልዉና ለማስቀጠል የተቋቋመዉ ጊዜያዊ ቦርድ ባለፋት አምስት ወራት ያከናወናቸዉን ተግባራት ለጠቅላላ ጉባኤዉ አባላት ይፋ አድርጓል።

‎ጊዚያዊ ቦርዱ ላለፋት ወራት በዋናነት የክለቡን የፋይናንስ ህልዉና ለማስቀጠል በስፋት ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሊቀመንበር አቶ ነሲቡ ጫኮ፣ የክለቡን የፋይናንስ ስርአት ለማስተካከል ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል።

‎በዚህም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በዓመት 200 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑ ተነግሯል።

‎የሞሀ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማህበር 80 ሚሊዮን ብር፣ ዳሸን ባንክ 200 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢጂአይ ኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን ብር በየዓመቱ ለስፖርት ማህበሩ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

‎ጊዚያዊ ቦርዱ ከቤኔፊካ እግር ኳስ ክለብ ጋር በታዳጊዎች ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሱም በጉባኤዉ ተመላክቷል።

‎ጉባኤዉ በበጀት ዓመቱ በነበረው አጠቃላይ የማህበሩ ሥራ አፈጻጸም ላይ ተወያይቶ ለቀጣዮች ዓመታት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በዚሁ ስብሰባ አዲስ የስታዲየም ዲዛይኑን ይፋ አደረጓል።


ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አዲስ ለሚያስገነባው ስታዲየም ዲዛይኑን ይፋ ያደረገው በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ባለው የ2019 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።

ክለቡ ቋሚ ሀብት እንዲኖረዉ እና በሁለት እግሩ እንዲቆም ለማድረግ ሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ከቢሾፍቱ ወደ ሞጆ በሚወስደዉ መንገድ ላይ የሚገኘዉን ሰፊ ቦታ የስፖርት ማህበሩ እንዲጠቀም በስጦታ አበርክተውለታል።

ቦታው 32 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት እንዳለውም ተገልጿል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail