
የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በድሬደዋ ስታዲዮም ከቀኑ 10 ሰዓት ከ 30 ለገሃሬ ከ ገሱባ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል
የ2018 የውድድር ዓመት የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ከተማ በትናትናው እለት ታቴኖ ሮያል ሆቴል የተካደ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 5 እስከ ነሐሴ 3 በሚካሄደው ውድድር የስያሜ ማሻሻያ በማድረግ «የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና» በሚል መጠርያ ውድድሩ እንደሚከናወን ተገልጿል።

በወንዶች በሚካሄደው ውድድር በወጣው የእጣ ድልድል መሰረትየ
በምድብ 1: ለገሀሬ፣ ዲክሲስ፣ ገሱባ ከተማ፣ አራዳ ክ/ከተማ
በምድብ 2: ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ መቱ ከተማ፣ ምዕራብ አባያ፣ ባምባሲ ቤላ አገሩ
በምድብ 3: ኡርጂ ቀፊራ፣ ቦረና፣ ቃኘው፣ መንቆረር
በምድብ 4: ጊምቢ ከተማ፣ ትግራይ ዋልታ ፖሊስ፣ ወረኢሉ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ
በምድብ 5: ፈረንሳይ ለጋሲዮን፣ ቡልዲግሉ ዙምባራ፣ አሳኢታ ወረዳ፣ ሑጻ ቆላ ገረዓልታ
በምድብ 6: ሽራሮ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ሲርጢ፣ አርባምንጭ ዙርያ
በምድብ 7: ሐረር ዩናይትድ፣ ቴፒ ከተማ፣ ቡርታ፣ አጄ
በምድብ 8: ጊምቦ ዳዲበን፣ ራማ ዓዲ አርባእተ፣ ኬሌ ከነም፣ ወሊሶ ከተማ
በምድብ 9: ሀደሮ ከተማ፣ አውራ ወረዳ፣ ሶማሌ ፖሊስ፣ ማሻ ወረዳ
በምድብ 10
ሐረር ከተማ ቢ፣ ባምባሲ ቤልማሊ፣ እንደጋኝ ሻርጋሮቹ፣ ሳቢያን ኅብረት
በምድብ 11
ሳንቢቱ፣ ጉለሌ ክ/ከተማ፣ ሁለት እጁ እነሴ የተደለደሉ መሆናቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና በሴቶች ውድድር ደግሞ
በምድብ 1: አርባምንጭ፣ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን፣ ተስፋ አብሮ አደግ፣ ምድረገነት ሽረ
በምድብ 2: ጋንታ ቢኤም፣ ሐረር ከተማ፣ ጅማ ከተማ፣ ኒውሆፕ
በምድብ 3: አብዲ ቦሩ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደልደላቸው ታውቋል
