(ከምስጋናው ታደሰ ጋር ያደረገው ቆይታ)

ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት የተለያየው ኢትዮጵያ ቡና አንጋፋውን አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌን በሁለት ዓመት ውል በዛሬው ዕለት አስፈርሞታል።

በተጨዋችነት ዘመኑ በቅ/ጊዮርጊስና በኢትዮጵያ ብ/ቡድን ስመ ገናና የነበረው ገ/መድህን በአሰልጣኝነት ዘመኑም በርካታ ክለቦችን አሰልጥኖ ስኬታማነቱን ማስመስከር ችሏል። ከሶስት የተለያዩ ክለቦች (ከጅማ አባጅፋር፣ መቀሌ 70 እንደርታ እና ከኢትዮጵያ መድህን) ጋር የፕሪሚየር ሉጉን ዋንጫ ያነሳ ብቸኛው አሰልጣኝ ነው።

አሰልጣኝ ገ/መድን ለቡና ዛሬ ማምሻውን ፊርማውን በይፋ ካኖረ በኋላ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተከታዩን ቆይታ አድርገን ነበር።

ጥያቄ፦ እንደምን አመሸህ ገሬ?

ገ/መድን፦ እግዚአብሔር ይመስገን! እንዴት አመሸህ ምስጌ?

ጥያቄ፦ ስምህ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርተሃል…

ገ/መድን፦ ልክ ነህ የሚፈልጉኝ ክለቦች የነበሩ ቢሆንም ምርጫዬ ግን ቡና ሆኗል። በነገራችን ላይ ዜናው ቀን ላይ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ሲወጣ ገና ፊርማዬን አላኖርኩም ነበር። የወረቀት ጉዳዮች አልቀው በይፋ ፊርማዬን ያኖርኩት ቅድም አንተ የደወልክልኝ ሰዓት አመሻሹ ላይ ነበር። እዛ ፕሮግራም ላይ ስለነበርኩ ነው ስልክህን ያላነሳሁልህ፤ ለዛ ነው ስጨርስ መልሼ የደወልኩልህ…

ጥያቄ፦ ከቡና በፊት እኮ ስምህ በስፋት ሲነሳ የነበረው ከፋሲል ከነማ ጋር ነበር…

ገ/መድን፦ ልክ ነህ…ፋሲሎች አናግረውኝ ነበር። ሁሉም እንደሚያውቀው ፋሲል ለብ/ቡድን ጭምር ተጨዋቾችን የሚያስመርጥ ትልቅ ክለብ ነው። በዛ ክለብ ውስጥ መስራት የማይፈልግ አሰልጣኝ አለ ብዬ አላስብም፤ እኔ ግን ኢትዮጵያ ቡናን ልመርጥ ችያለሁ።

ጥያቄ፦ እኔ እንደውም የሰማሁት ፋሲሎች 15 ሚሊዮን ብር የፊርማ ክፍያ አቅርበውልህ እንደነበር ነው…ቡናን የመረጥከው ታዲያ ከዚህ የተሻለ ገንዘብ አቅርቦልህ ነው ማለት ነው?

ጥያቄ፦ ኖኖኖ…እንደዛ አይደለም። ምስጌ እኔና አንተ ረጅም ዓመታት የምንተዋወቅ ሰዎች ነን። ዕውነቱን ነው የምነግርህ፤ ፋሲሎች አናግረውኛል። በጣም ጥሩ ሰዎች ናቸው። በዚህ አጋጣሚ አክብረውኝ ስለመጡ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ብዙ ብንነጋገርም 15 ሚሊዮን ብር የፊርማ ክፍያ የተባለው ግን ትክክል አይደለም። በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተነጋገርን እንጂ የገንዘቡ ጉዳይ ላይ ገና አልደረስንም ነበር። ቡናም ከዚህ በላይ አልሰጠኝም።

ወደ ዕውነታው ስንመጣ ቡናዎች ያናገሩኝ ከፋሲል አስቀድመው ነው። እኔም ውድድሩ ሲያልቅ ቅድሚያ የምደራደረው ከእነሱ ጋር እንደሆነ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ስለዚህ ያንን ቃሌን መጠበቅ ነበረብኝ። ፋሲሎች ያናገሩኝ ለቡና አመራሮች ቃል ከገባሁላቸው በኋላ ነው። ያ ካልተሳካ ግን በቀጣይነት ከእነሱ ጋር የጀመርኩት ድርድር ሊቀጥል ይችል ነበር። የነገርኳቸውም ይሄንኑ ነው።

ጥያቄ፦ እሺ ኢትዮጵያ ቡና ምን ያህል የፊርማ ክፍያ ከፈለህ?

ገ/መድን፦ (ከት ብሎ ስቆ) አንተ ኢትዮ ኤፍ.ኤም 107.8 ምን ያህል ይከፍልሃል?

ጥያቄ፦ ምን ያደርግልሃል?

ገ/መድን፦ (አሁንም እየሳቀ) የእኔስ ታዲያ ምን ያደርግልሃል?… ወደ ቁምነገሩ ስንመጣ ግን መቼስ በነፃ ነው የምሰራው አልልህም… የሚገባኝን ሊከፍሉኝ ተስማምተን ነው የፈረምኩት። ከሁሉም በላይ ግን አስፈላጊው ነገር ክለቡን ወደ ሻምፒዮናነት መመለሱ ላይ ነው። ሁለታችንም ወገኖች ትኩረት ሰጥተን ለረጅም ጊዜያት ስንነጋገር የነበረው በዚህ ጉዳይ ላይ ነው። ውጤቱ እስከመጣ ድረስ እኮ ገንዘቡም አብሮ ይመጣል። ቅድሚያ የሰጠነውም ውጤቱ ላይ ነው…

ጥያቄ፦ ብዙ አሰልጣኞች “ቡናን ማሰልጠን ከደጋፊው ብዛት አንፃር ጫናው ከባድ ነው” ይላሉ፤ ትስማማለህ?

ገ/መድህን፦ ዕውነት ለመናገር የአሰልጣኝነት ህይወት በጣም ከባድ ነው። የትኛውንም ክለብ ብትይዝ ጫናው ከባድ ነው። እንደ ቡና ዓይነት የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት የሆነ ክለብ ስትይዝ ደግሞ ዕውነት ነው ጫናና ግፊቱ ከዚህም የባሰ ነው። ነገር ግን እኔ በባህሪዬ ጫና የመሸከም አቅም አለኝ ብዬ አስባለሁ። ጅማ አባ ቡና እና መቀሌም እኮ በርካታ ደጋፊዎች አሏቸው። ያንን ተቋቁሜ ነው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሁት። ስለዚህ በዚህ ዙሪያ ብዙም ስጋት የለብኝም።

ሌላው ለመግለፅ የምፈልገው ነገር በክለብ ደረጃ ለቅ/ጊዮርጊስ ልጫወት እንጂ በአሰልጣኝነት ዘመኔ እኮ ቡናን አሰልጥኛለሁ። አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ነው የመጣሁት። ደጋፊውን በደንብ አውቀዋለሁ። ለክለቡ ህይወቱን የሚሰጥ ምርጥ ደጋፊ ነው። ለክለቡ ይዘምራል፤ በተቃራኒው ደግሞ በተጋጣሚው ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር የተቻለውን ሁሉ ጫና ይፈጥራል። ይሄ በየትኛውም ክለብ ውስጥ ያለ ነው። የቡና ደጋፊ በአሰልጣኞች ቡድን አባላትም ላይ ሆነ በክለቡ አመራሮች ላይ ተቃውሞውን የሚያሰማው እኮ ከውጤት መናፈቅ አንፃር እንጂ የግል ጥላቻ ኖሮት አይደለም። ይሄ ደግሞ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድን በመሳሰሉ የዓለማችን ታላላቅ ክለቦች ሁሉ የሚያጋጥም ነው። የቡና ደጋፊ እኮ ከሜዳ ውጪ ሰላማዊ ነው…

ጥያቄ፦ በዚህ አጋጣሚ ደጋፊውን ምን ትለዋለህ?

ገ/መድን፦ ያው ለእነሱ ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ልነግራቸው ነው የምፈልገው። ቡናን ወደ ሻምፒዮናነት ለመመለስ የእኔና የባልደረቦቼ ጥረት ብቻ ሳይሆን የእነሱ ድጋፍም ያስፈልገናል። አንዳንዴ ነገሮች ጥሩ ባይሆኑ እንኳን በሰከነ ሁኔታ እየተመካከርን እንድንጓዝ ነው የማስበው።

ጥያቄ፦ አሁን ቡናን በይፋ ተረክበሃል…ክለቡን የሚለቁና የሚመጡ ተጨዋቾች አሉ?

ገ/መድን፦ ይሄ ግድ ነው። ሊጉ ላይ እንደመቆየቴ መጠን የራሴን ክለብ (መድህንን) ብቻ ሳይሆን የሌሎች ክለቦችን ክፍተቶችም ስገመግም ነበር። ቡና ውስጥ ኮንትራታቸውን የጨረሱ እና የውጪ ሙከራ ላይ ያሉ ልጆች አሉ። ኮንትራት ከጨረሱት ውስጥ የምፈልጋቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ለመቀጠል ፈቃደኛ ከሆኑ የተወሰኑት ሊቀጥሉ ይችላሉ። ከዛ በተረፈ ከቦርዱ ጋር መነጋገር ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ክለቡ ክፍተቶች ባሉበት ቦታዎች ላይ ቢመጡ ሊያግዙን ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ተጨዋቾች ለማስፈረምና ጠንካራ ቡድን ለመስራት እሞክራለሁ።

ጥያቄ፦ ክለቡን በዛሬው ዕለት በይፋ ስትረከብ ዋንኛ ግብህ ምን ሆኖ ነው ሀላፊነቱ የተሰጠህ?

ገ/መድን፦ ከቦርዱ ጋር ብዙ አውርተናል። የሁለት ዓመት ኮንትራት ነው የተፈራረምኩት። ለራሴ ማጋነን ሳይሆን በጫና ውስጥ መስራት የምችል ሰው ነኝ። ሁሉም እንደሚያውቀው ከዚህ ቀደም ከሶስት ክለቦች (ከጅማ፣ መቀሌ እና መድን) ጋር የሊጉን ዋንጫ አንስቻለሁ። አሁን ደግሞ ወደ ቡና የመጣሁት አራተኛው የሊጉ ሻምፒዮን ክለቤ ላደርገው ነው። ከተሳካልን በመጀመሪያው ዓመት…ካልሆነልን ደግሞ በሁለተኛው ዓመት። በዚህ ጉዳይ ከቦርድ አባላቱ ጋር በሰፊው ከተነጋገርን በኋላ ነው ተስማምተን የፈረምኩት። በዚህ አጋጣሚ ደጋፊውም ከጎናችን እንዲሆን ጥርዬን አቀርባለሁ።

ጥያቄ፦ በጣም አመሰግናለሁ ገሬ!!

ገ/መድን፦ በስማበለው ከሚናፈሱት ወሬዎች ውጪ ቀጥታ ከእኔ አንደበት ለመስማት ላደረግከው ሙከራ እኔም በጣም አመሰግናለሁ !

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *