
ከ17 አመት በታች ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ በአበበ ብቂላ ስታዲዮም የመልስ ጨዋታውን ከዛምቢያ አቻው ጋር ያደረገው የሴቶች ብሔራዊ ቡድናችን በሜዳው ላይ አቻ በመለያየቱ ለዓለም ዋንጫ ሳያልፍ ቀርቷል።
በመጀመሪያው ጨዋታ ዛምቢያ ላይ 2ለ1 የተሸነፈው ቡድናችን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ባደረገው በዛሬው ጨዋታ በ46ኛው ደቂቃ ፕሪሽየስ ምዌዋ ባስቆጠረችው ግብ 1ለ0 ሲመራ ቆይቶ ፤ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃ ሲቀረው በ88 ኛው ደቂቃ ላይ በሜዳውና በደጋፊው ፊት ከመሸነፍ የሚያድነውን ብቸኛና አቻ የምታደርገውን ግብ ምኅረት አየለ ባስቆጠረችው ግብ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በመሆኑም ብሔራዊ ቡድናችን በድምር ውጤት 3ለ2 ተሸንፎ ወደ ዓለም ዋንጫ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል ።
በኳስ ጨዋታ ማሸነፍና መሸነፍ ያለ ቢሆንም ውጤቱ ይበልጥ ታዳጊዎች ላይ መስራት እንዳለብን የሚያሳይ ነው፤በሴቶች እግር ኳስ ከእኛ ኋላ የጀመሩ ሀገሮች እንደ ዛምቢያ ያሉ ሀገሮች ለዓለም ዋንጫ ሲያልፉ እኛ በዋናው የሴቶች ቡድንም ለአፍሪካ ማለፍ ተስኖናል ። ይህ ውጤትም የነገውን የዋና ቡድን የሚተኩ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚያሳይ ነው ።በአሁኑ በርካታ ሜዳዎችም አሉ ፤የስፖርት ማዕከሎችም በብዛት ተከፍተዋል ።ክለቦችም ለስፖርተኞቻቸው ፣አስልጣኞችንና የቡድኑን አባላት ጭምር የሚከፍሏቸው ክፍያ አንድ ባችለር፣ማስተር፣ዶክተር፣ተባባሪ ፕሮፌሰር፣እረዳት ፕሮፌሰር ከብዙ ልፋትና ድካም በኋላ ፕሮፌሰር ሆኖ ያማያገኘውን ደመወዝ መንግሥት ለስፖርቱ ብሎ ከሚመድበው ገንዘብ በጥሩ ሁኔታ እየተከፈላቸው ነው የሚገኙት ፤በፊት በእኛ ጊዜ ከስልጠና በስተቀር የምናገኘው ነገር የለም ፍቅር ስላለን የአውቶብስ መሳፈሪያ የሚሰጠን አተን ፍቅሩ ስለነበርን በእግራችን እየሄድን ነበር ስልጠና እንወስድ የነበረው ፤ከእኛ በኋላም ያሉ ታዳጊዎች ላብ መተኪያ ፣የስፖርት ትጥቅና ትራንስፖርት እንኳን አያገኙም ነበር ፤አሁን ከበፊቱ በብዙ ነገር የተለየ ቢሆንም በፊት የነበረው ስፖርት ከአሁኑ የተሻለ ነበር ፤እግር ኳሳችን አሁን ይብስ ብሎ ዳዴ ማለቱን አላቆመም ፤ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት በደርግ ጊዜ እግር ኳስን የሚይዝ ክለብ አምስት ስፖርቶችን በግድ እንዲያዝ ይደረግ ነበር ፤አሁን ግን ይህ ሁኔታ የለም ፤ከእግር ኳስ በስተቀር ሌላው ስፖርት ሞቷል ማለት ይቻላል፤ለዚህ ደግሞ ያለፈው መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው የስፖርት ፖሊሲ ነው ፤ይህ የስፖርት ፖሊሲ ሆዳም ሙሁራኖች የወያኔ መንግሥትን ለማስደሰት ብለው ያወጡት እንጅ የስፖርት ቤተሰቡ መክሮና ዘክሮ ያወጣው አይደለም፤ ስለዚህ ፖሊሲው እንደገና መመርማር ተተኪዎችን ለማፍራት የታዳጊ ፕሮጀክቶች ስልጠና በስፋት እንዲካሄድ ማድረግ በዋንኛነት ሊተኮርበት የሚገባ ነው።ለዚህ ደግሞ ሁሉም ወገኖች ለስፖርቱ ተጠያቂ ነው ። ስለዚህ የሚመለከተው አካል ፤ለስፖርቱ ተብሎ የሚወጣውን ወጪ እግር ኳስን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ስፖርቶች መገምገምና መፈተሽ እንደሚኖርበት ሳናሳስብ አናልፍም ።
