
መድፈኞቹ ለኒውካስትል አማካይ 120 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሁም ለአስቶን ቪላ ኮከብ 130 ሚሊዮን ፓውንድ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃደኞች መሆናቸው ታውቋል።

ሚኬል አርቴታ ሁለቱንም ተጫዋቾች የፕሪሚየር ሊጉን ጠንካራውን የመሃል ሜዳ ለመገንባት ባቀደው እቅድ ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወትልኛል በማለት ሁለቱን ተጫዋቾ ለአምስት አመት ያህል ለማስፈረም መቃረቡ ታውቋል ።
ክለቡ ከተጫዋቾቹ ጋር ከስምምነት የደረሰ ሲሆን ከክለቦቹ ጋር አሁንም ድርድሩ እንደቀጠለ ነው ።በሌላ በኩል ክለቡ የክለብ ብሩጅን ተጨዋች ክሪስቶስ ዞሊስን በ £35 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ተቃርቧል ።
ክሪስቶስ ዞሊሰን ወደ ቤሺክታሽ የሚያመራውን የሌአንድሮ ትሮሳርድ ምትክ ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል።
ክለቦቹ በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨዋቹን ከስምምነት ለመድረስ ተቃርበዋል ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤመርሰን ንዋኔሪ ከአርሰናል ጋር ለመቆየት ተስማምቷክ።
ረጅም ድርድር ካደረገ በኋላ አማካኝ ተጫዋች በሰሜን ለንደኑ ክለብ ውስጥ ይቆያል ተብሏል።
ተጨዋቹ ለማስፈረም ከቼልሲና ከማንቸስተር ሲቲ ፍላጎት እንደነበረ ተዘግቧል፣ ነገር ግን ተጫዋቹ በአርሰናል ደስተኛ ስለሆነ ለመቆየት መርጧል።
ኤመርሰን ለአርሴል ለወደፊቱ ትልቅ ተስፋ ያለው ተጨዋች ነው ተብሏል።
