
𝐁𝐈𝐆 𝐁𝐎𝐌𝐁𝐀 𝐅𝐎𝐑 𝐔𝐍𝐈𝐓𝐄𝐃። 🔥🇧🇪
ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጂየማዊው አማካይ ተጨዋች ዮሪ ቲሌማንስን ከአስቶን ቪላ በ36 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ተቃርቧል።
አማካይ ተጨዋቹን ዩናይትድ ሲያስፈርም በኮንትራቱ ውስጥ ውሉን የማፍረስ አንቀጽ እንዳለው ታውቋል።
ቤልጂየም ከዓለም ዋንጫ ከወጣች በኋላ ውይይቶቹ በአሁኑ ወቅት በፍጥነት እየተካሄደ ይገኛል ።
ቲሌማንስ ከ2023 ጀምሮ ከሌስተር ሲቲ በነፃ ዝውውር አስቶን ቪላ ከተቀላቀለ ጊዜ ጀምሮ በቪላ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ነው፣ለክለቡ 134 ጨዋታዎችን አድርጓል፣ 10 ግቦችን አስቆጥሯል።
ቪላ ሁለት ጊዜ ለቻምፒዮንስ ሊግ ያለፈ ሲሆን፣ በውድድሩ ላይ ሩብ ፍፃሜ ላይ ደርሷል ፤ባለፈው የውድድር ዘመን በኡናይ ኤምሪ ስር የዩሮፓ ሊግን አሸንፏል፣ ቲሌማንስ ከፍሪበርግ ጋር በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
ቲሌማንስ ቪላን ከመቀላቀሉ በፊት በሌስተር ሲቲ የኤፍኤካፕ ዋንጫና የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ አሸንፏል።
ዩናይትድ የቼልሲውን አማካይ አንድሬ ሳንቶስን ለማስፈረም £50 ሚሊዮን ስምምነት ላይ ደርሶ ነበር፣ ነገር ግን ቲሌማንስን ለማዛወር ክለቡ የወሰነው በጣሊያን የአትላንታ አማካይ ተጨዋች የሆነውን ኤደርሰንን ለማዛወር የሚያደርገው ጥረት ውድቅ ማድረጉን ከዘገበ በኋላ ነው።
ዩናይትድ በዓለም ዋንጫው ላይ ለአገሩ ብራዚል የተጫወተውን ብራዚላዊውን ኢንተርናሽናል ለማስፈረም ያሰበውን በሜዲካል ምክንያት ውድቅ ካደረገ በኋላ ቴሊማንስን በ£38 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት ከቪላ ለመግዛት በቅቷል፣ቴሊማንስ በክለቡ ውስጥ የአራት ዓመት ውል ለመፈረም እና ለተጨማሪ 12 ወራት የሚቆይበትን ጊዜ ለማራዘም መስማማታቸው ታውቋል።
