
አርጀንቲናዊው የሊቨርፑል አማካይ አሌክሲስ ማክአሊስተር ወደ ሪያል ማድሪድ የሚደረገው ዝውውር እየተጠናቀቀ ነው። የስፔኑ ክለብ የመሀል ሜዳ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና በዝውውር እቅዳቸው ውስጥ እንደሚያካትቱት በተደጋጋሚ ከዚህ በፊት ሲገለጽ ቆይቷል ።
ማክአሊስተር ከሊቨርፑል ጋር እስከ ሰኔ 2028 (እ.አ.አ) የሚቆይ ውል ነበረው፣ ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን ለማዘዋወር ትልቅ የገንዘብ ወጪ ማውጣት ይጠበቅበታል።ለዚህም ይመስላል ሊቨርፑል ከ£60/65m ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የውል ማፍረሻ ውል ይፈልጋል – ይህ ለቀዮቹ የመጀመሪያ የድርድር ዋጋ ነው። በዚህ በኩል ከስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ እንዲያውም የህክምና ምርመራውን ከ24 እስከ 48 ሰዓታት ውስጥ ሊያጠናቅቅ እንደሚችልና በአምስት አመት ውል ለሪያል ማድሪድ ለመፈረምና በግል ውል ዙሪያም መስማማቱ ተጠቁሟል ።
የተጫዋቹ አባትና ወኪል የሆኑት በሰጡት አስተያየት አሌክሲስ በሊቨርፑል ቤት በጣም ደስተኛ እንደሆነና አሁን ግን ወደ ሪያል ማድሪድ ለማምራት ውይይቶች እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።
ማካልስተር በሪያል ማድሪድ ውስጥ ሲፈለግ የቆየው ሉካ ሞድሪች ወደ ኤሲ ሚላን ከማምራቱ በፊት ነበር፣ ማድሪድ የአማካይ ክፍሉን ለማጠናከር ከተመለከታቸው ቁልፍ ተጫዋቾች መካከል ማክአሊስተር አንዱ እንደነበር ይታወሳል።
ሊቨርፑል ተጫዋቹን ለመልቀቅ በተደጋጋሚ ፍላጎት እንደሌለው ሲገልጽ ቆይቶ ነበር።
