
በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ ድል እና አዲስ የግል ምርጥ ሰዓቶች አስመዝግቧል
በዓለም አቀፍ ደረጃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 10ኛው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ በአስደናቂ ፉክክር፣ በአዳዲስ የዓለምና የውድድር ክብረወሰኖች መሻሻል እንዲሁም በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ ውጤት ታጅቦ ተጠናቋል።
በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ወጣትና ተስፈኛ የሀገራችን አትሌቶች ፈታኝ በሆነው መድረክ ላይ የራሳቸውን ምርጥ ሰዓት ማሻሻል የቻሉበትን አስደናቂ ብቃት አሳይተዋል።

የሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች የአሸናፊነት መንፈሳቸውን በተግባር አስመስክረዋል።
ወጣቷ አትሌት አለሽኝ ባወቅ አስደናቂ ብቃትና የመጨረሻ መስመር ፍጥነት በማሳየት 8:23.81 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በሁለተኛነት አጠናቃለች።

አትሌት አለሺኝ በፔሩ ሊማ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት ሻምፒዮና የ3ሺ ሜትር አሸናፊ መሆኗን የሚታወስ ነው።
ሌላኛዋ ተስፈኛ አትሌት ሰናይት ጌታቸው እስከ መጨረሻው ሰከንድ ድረስ ብርቱ ፉክክር በማድረግ 8:24.02 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የክብር መድረክ ላይ መውጣት ችላለች።

በዚሁ የርቀት ውድድር ላይ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም አትሌት ፍረወይኒ ኃይሉ 5ኛ ፣አትሌት ዓይነአዲስ መብራቱ 6ኛ ፣አትሌት ሚዛን ዓለም 7ኛ ፣አትሌት የኔነሽ ሽመክት 10ኛ ፣አትሌት በርነሽ ደሴ 12ኛ እና አትሌት ብርቄ ሐየሎም 14ኛ ወጥተዋል ።
የወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ወጣቱ አትሌት ቢኒያም መሀሪ ጠንካራ ፉክክር በማድረግ ውድድሩን በ12:58.37 6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኬይሪ በጂጋ 13:07.
