– ፕሪምየር ሊግ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች የካፍ ኤ ላይሰንስ ያስፈልጋቸዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሰሩ ዋና ምክትል አሰልጣኞች የካፍ ኤ ላይሰንስ ሊኖራቸው ይገባል አለ። የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ዋና እና ምክትል አሰልጣኝ የካፍ ላይሰንስ ካላቸው የመቅጠር ግዴታ የሚኖርባቸው ሲሆን ሁለተኛ (ተጨማሪ) ምክትል አሰልጣኝ መቅጠር ለሚፈልጉ ዝቅተኛ የአሰልጣኝነት ደረጃ የካፍ ቢ ላይሰንስ ሊኖራቸው ይገባል ብሏል። ለግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ደግሞ ዝቅተኛው ሲ ላይሰንስ በግዴታነት ተቀምጧል ።
ከዚህ ሌላ የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ ለዋና እና ምክትል አሰልጣኝ – ቢ ላይሰንስ ፣ ለግብ ጠባቂ አሰልጣኝ – ሲ ላይሰንስ መኖር አለበት።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ለዋና እና ምክትል እንዲሁም ግብ ጠባቂ አሰልጣኝ – ሲ ላይሰንስ ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዋና አሰልጣኝ – ቢ ላይሰንስ፣ ምክትል አሰልጣኝ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ – ሲ ላይሰንስ ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ዋና አሰልጣኝ፣ ምክትል አሰልጣኝ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ – ሲ ላይሰንስ።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚወዳደሩ ክለቦች ከዋና እና ምክትል አሰልጣኝ መካከል አንዷ ሴት መሆን ይኖርባታል ሲል መመሪያ አውጥቷል።
