
የ10 ኛው ስቴጅ ውድድር በታደይ ፖጋቻር (Tadej Pogačar) ብቸኛና አስደናቂ የበላይነት ተጠናቋል። ውድድሩ የተካሄደው በፈረንሳዮች ብሔራዊ ቀን (ባስቲል ዴይ) ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ሲሆን፣ ከባድ የተራራ ላይ ፉክክር የታየበት ውድድር ነበር።

የዛሬው ውድድር 166.6 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ሲሆን መነሻው ከአውሪላክ (Aurillac) አድርጎ
ረሻው ሌ ሊዮራን (Le Lioran) መጨረሻውን ያደረገ ነበር።
ውድድሩ 7 ደረጃ ያላቸውን ከባድ ተራራማ ሽቅብ ቁልቁለቶችን ያካተተ ሲሆን፣ በጥቅሉ 3,800 ሜትር ከፍታን መውጣትን የሚጠይቅ አድካሚ ነበር።
ፖጋቻር ውድድሩን ለማጠናቀቅ 15.5 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ከተቀናቃኞቹ በመገንጠል ባደረገው ፈጣን በረራ ዋና ተቀናቃኙ ዮናስ ቪንጌጋርድን (Jonas Vingegaard) ጨምሮ ሌሎችን በመቅደም የቢጫ ማሊያውን ከወዲሁ ለአራተኛ ጊዜ በማሸነፉ ለማረጋገጥ በቅቷል፤

በዚህ ውድድር ከአንድ እስከ ሦስት የወጡት
1ኛ ደረጃ (አሸናፊ)፦ ታደይ ፖጋቻር (Tadej Pogačar – UAE Team Emirates-XRG) — ውድድሩን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ 58 ደቂቃ ከ 08 ሰከንድ ፈጅቶበታል።
2ኛ ደረጃ፦ ሬምኮ ኤቨንፖል (Remco Evenepoel) — በ32 ሰከንድ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ወጥቷል።
3ኛ ደረጃ፦ ፖል ሴይክሳስ (Paul Seixas) ሆኗል።
