ኢትዮጵያኖች የራሳችሁን ሰዓት ከማሻሻል ውጭ አልቀናቸውም

የለንደን ዳይመንድ ሊግ (London Diamond League) ትላንት በተካሄደው ውድድር ጆሽ ኬር (Josh Kerr) የዓለም ክብረ ወሰንን የሰበረበት ድንቅ ምሽት ነበር። ኬር የ 1 ማይል ርቀትን በ 3:42.66 በመጨረስ የአልጄሪያዊውን ሂሻም ኤል ጉሩጅን የቆየ ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።
ሌሎች የትላንቱ አበይት ውጤቶች፦
የሴቶች 800 ሜትር፦ ኪሊ ሆጅኪንሰን (Keely Hodgkinson) በ 1:56.21 አንደኛ በመሆን አሸንፋለች።
የሴቶች 200 ሜትር፦ ጁሊየን አልፍሬድ (Julien Alfred) በ 21.66 በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።
የወንዶች 100 ሜትር፦ ካይንሶላ አጃዪ (Kayinsola Ajayi) በ 9.84 ሰከንድ አሸንፏል።
የወንዶች 400 ሜትር፦ ሬይ ቤንጃሚን (Rai Benjamin) አንደኛ ሲወጣ፣ ማቲው ሃድሰን-ስሚዝ ሁለተኛ ሆኗል።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ያስመዘገቡ ሲሆን፣ ፅጌ ዱጉማ በ 800 ሜትር 3ኛ ደረጃን በመያዝ ብቸኛውን የመድረክ (ፖዲየም) ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። በተጨማሪም በሴቶች 3,000 ሜትር በርካታ አትሌቶች የግል እና የዓመቱን ምርጥ ሰዓቶቻቸውን አሻሽለዋል።

ለንደን ዳይመንድ ሊግ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል 5ኛ ሆና አጠናቀቀች፤ ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር 3ኛ ደረጃን ያዘች ።

የ2026 የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ 11ኛ መዳረሻ ውድድር በለንደን በከፍተኛ ፉክክር ተካሂዶ ሲጠናቀቅ፣ በሴቶች 3,000 ሜትር አውስትራሊያዊቷ ጀሲካ ሀል 8:24.69 በመሮጥ ድል ቀንታለች።
ኢትዮጵያዊቷ ፋንታዬ በላይነህ ደግሞ የግል ምርጥ ሰዓቷን 8:26.98 በማሻሻል 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያውያን ወጣት አትሌቶችም የግል ምርጥ እና የዓመቱ ምርጥ ሰዓቶቻቸውን በማሻሻል ተስፋ ሰጪ ብቃት አሳይተዋል።
ፋንታዬ በላይነህ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል የአለም ደረጃ ውድድር ላይ ተወዳዳሪነቷን እያጠናከረች መሆኗን አሳይታለች።
በተመሳሳይ መዲና ኢሳ እና ሒሩት መሸሻ የዓመቱን ምርጥ ሰዓት ሲያስመዘግቡ፣ ማርታ አለማየሁም የግል ምርጥ ሰዓቷን አሻሽላለች።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ውጤት – 3,000 ሜትር
5ኛ – ፋንታዬ በላይነህ – 8:26.98 (PB)
8ኛ – መዲና ኢሳ – 8:27.99 (SB)
9ኛ – ሀዊ አበራ – 8:28.00
10ኛ – ማርታ አለማየሁ – 8:29.09 (PB)
12ኛ – ሒሩት መሸሻ – 8:32.04 (SB)
የሴቶች 800 ሜትር ፉክክር፣ ከኢትዮጵያ ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበረችው ፅጌ ዱጉማ 1:56.92 በመሮጥ 3ኛ ደረጃን በመያዝ መድረኩን አጠናቀቀች።
ይህም የ2026 የውድድር አመቷ ምርጥ ውጤት ነው።
ፅጌ ዱጉማ በጠንካራ የመጨረሻ 200 ሜትር ሩጫ 3ኛ ደረጃዋን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የመድረክ ውጤት አስመዝግባለች።
የለንደን ዳይመንድ ሊግ ለኢትዮጵያ አትሌቶች የተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
ምንም እንኳን በ3,000 ሜትር የመድረክ ቦታ ማግኘት ባይቻልም፣ በርካታ አትሌቶች የግል ምርጥና የዓመቱን ምርጥ ሰዓት በማሻሻል ወደ ቀጣይ የዓለም ውድድሮች በጥሩ አቋም መግባታቸውን አሳይተዋል።
