በአሜሪካው የዓለም ዋንጫ ማጠናቀቂያ ላይ ዊሊያም ሳሊባ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ አርሰናል በአስቸኳይ የተከላካይ መስመር (ባክአፕ) ለማጠናከር አዲስ ተጨዋች እየፈለገ ነው።

አርሰናል ለአስቸኳይ ምትክ የአስቶን ቪላውን ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳን ለማስፈረም እያጠና ነው። በተጨማሪም የሪያል ሶሴዳድን ተከላካይ ለማስፈረም እየፈለገ ነው።

ዊሊያም ሳሊባ ባጋጠመው ከባድ የጀርባ ጉዳት ምክንያት ቀዶ ጥገና እንደሚያደርግና ከ4 እስከ 6 ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ Lequipe እና NBC  ይፋ አድርገዋል።

አርሰናል የአስቶን ቪላውን እንግሊዛዊ ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳን የሳሊባ ቀጥተኛ ምትክ አድርጎ ለመውሰድ የመጀመሪያ ፍላጎቱን አሳይቷል። ሆኖም አስቶን ቪላዎች ተጫዋቹን በቀላሉ የመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም።

ክለቡ ሌላ አማራጭ አድርጎ የያዘው የስፔኑን ሪያል ሶሴዳድ የመሐል ተከላካይ በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል።

አርሰናል ባለፈው የውድድር ዓመት በውሰት አብሮት የቆየውን ሁለገብ ተከላካይ ፒየሮ ሂንካፒን በ34.5 ሚሊዮን ፓውንድ በቋሚነት አስፈርሞታል። እሱም በሳሊባ ቦታ ላይ እንደ ትልቅ አማራጭ ይታያል።

በተጨማሪም በአጥቂ መስመር ላይ አርሰናል አርሰናል ግሪካዊውን የክንፍ አጥቂ ክሪስቶስ ትዞሊስን (Christos Tzolis) ከክለብ ብሩዥ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል። ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራ እንደሚያደርግ ታውቋል። እሱም ወደ ቤሽክታሽ የተዛወረውን ሌአንድሮ ትሮሳርድን ይተካል ተብሏል።


ክለቡ ቀጣዩ ትልቅ ኢላማው ያደረገውን ሞርጋን ሮጀርስ (Morgan Rogers) የአርሰናል ዋነኛ የክረምቱ ኢላማ ሲሆን የአስቶን ቪላው ኮከብ ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ መልስ አርሰናል ይፋዊ ጥያቄ ለክለቡ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው። ይሁንና አስቶን ቪላ ተጫዋቹን ለመልቀቅ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ይፈልጋል። ፖል ስኮልስ ተጫዋቹ ወደ አርሰናል ማቅናትን እንደሚመርጥ ፍንጭ ሰጥቷል። 

ሞርጋን ሮጀርስን ለማስፈረም የአርሴናል የክብረወሰን ሰባሪ ሂሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

አርሰናል የ23 ዓመቱን የአስቶን ቪላና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ሞርጋን ሮጀርስን የክረምቱ ቁጥር አንድ የአጥቂ መስመር ኢላማው አድርጎታል።

ታዋቂው የዝውውር ዘጋቢ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጸው፥ አርሰናል ከተጫዋቹ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።

አርሰናል የቀድሞውን የዴክላን ራይስን የ£100 ሚሊዮን የክለብ የዝውውር ክብረወሰን የሚሰብር የ£105 ሚሊዮን የመጀመሪያ ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው።

አስቶን ቪላዎች ተጫዋቹ ባለፈው ህዳር ወር እስከ 2031 የሚያቆይ ውል በመፈረሙ ጠንካራ የድርድር አቋም አላቸው። ተጫዋቹን ለመልቀቅ እስከ £130 ሚሊዮን ይፈልጋሉ።

አርሰናል ባለፈው የውድድር ዘመን የማጥቃት ስልቱን በብዛት በቡካዮ ሳካ በኩል (43%) ያደላ ነበር፥ ሮጀርስን በግራ ክንፍ በኩል ክለቡ የሚጠቀም ከሆነ በማጥቃት በኩል እእእ ሚዛንኑን ለመጠበቅ ያስችለዋል ።

አርሰናል የኒውካስትሉ አማካይ ብሩኖ ጊማሬሽን (Bruno Guimaraes) ክለቡ ለማስፈረም በወኪሎቹ አማካኝነት በምስጢር ንግግር እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል። በብዙ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል፤ተጨዋቹም ኒውካስትልን መልቀቅ እንደሚፈልግ በመግለጹ ኒውካስትል በዝውውሩ ዋጋ ዙሪያ ድርድር እያደረገ ነው ።

በሌላ በኩል ፈረንሳዊው ግብ ጠባቂ ኢላን መሲሊየር ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ያለው ውል ማብቃቱን ተከትሎ በነፃ ዝውውር (Free Transfer) አርሰናልን በይፋ ተቀላቅሏል።

የ26 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ከለንደኑ ክለብ ጋር ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚራዘም የሁለት ዓመት ውል ተፈራርሟል።

መሲሊየር ለአሁኑ ከዳቪድ ራያ እና ከኬፓ አሪዛባላጋ በመቀጠል በሶስተኛ ግብ ጠባቂነት ነው ክለቡን የተቀላቀለው። ሆኖም ሁለተኛው ግብ ጠባቂ ኬፓ በዚህ ክረምት የሚለቅ ከሆነ ቀጥታ የራያ ዋነኛ ምትክ (ቁጥር ሁለት) ይሆናል።

«በእንግሊዝ ትልቁ ክለብና ከባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮናዎች ጋር በመቀላቀሌ ኩራት ይሰማኛል፤ ከዚህ ክለብ ጋር ዋንጫዎችን ለማንሳት አልችላለሁ» ሲል በአርሰናል ድረ-ገጽ ላይ ደስታውን ገልጿል።

የእሱ መምጣት የ20 ዓመቱ ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በውሰት ውል ወደ ሌላ ክለብ ሄዶ የመጫወት ዕድል እንዲያገኝ በር ከፍቶለታል።

የኤምሬትሱ ክለብ የቶተንሃሙን የቀድሞ ተከላካይ ማቲው አፕሰን የ18 ዓመት ልጅ ኤሊጃህ አፕሰንን (Elijah Upson) ከቶተንሃም አካዳሚ በነፃ ዝውውር አስፈርሞታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አርሰናል አጥቂውን ቪክቶር ጂዮኬሬስን በዝውውር ውስጥ በማካተት የጁሊያን አልቫሬዝን ዝውውር ለመጨረስ እያሰበ ባለበት ወቅት፥ ጋብሪኤል ጄሱስን ወደ ጣሊያን ክለቦች ለመሸጥ ድርድሮች እየተደረጉ ነበር። ይሁንና ዮኬረሽን አሁን ክለቡ የመሸጥም ሆነ የመለወጥ ፍላጎት የለውም፤አትሌቲኮም ቢሆን ከ150 እስከ 200 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጋል ፤አልቫሬዝም ቢሆን መዛወር የሚፈልገው አርሴናል ሳይሆን ባርሴሎና ነው፤ባርሴሎና ይህን ክፍያ ለመፈጸም አቅም የለውም ፤ስለዚህ ይመስላል አርሰናል ብራዚላዊውን አጥቂ ጋብሪኤል ጄሱስን በ20 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለመሸጥ ለጣሊያን ክለቦች ፍቃደኛ ሆኗል። እንደ ኤሲ ሚላንና ጁቬንቱስ ያሉ የጣሊያን ክለቦች ለመግዛት ፍቃደኛ ቢሆኑም ዋጋው እንዲቀነስላቸው እየተደራደሩ ነው።

የአስቶን ቪላ ዋና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬይ ማርቲኔሊን እንደሚፈልጉ ቢነገርም፣ አርሰናል ማርቲኔሊን ለመሸጥ ያለው ፍላጎት አናሳ ነው።

ስለ ጋብሪኤል ማርቲኔሊ ወደ አስቶን ቪላ ስለሚያደርገው ዝውውር የሚነገሩ ወሬዎች የተጋነኑና ትክክለኝነታቸው እጅግ ዝቅተኛ የሆነ የፈረንጅ ሀገር የሶሻል ሚዲያ ወሬዎች ናቸው።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *