ስዊዲን ላይ የጠፉት ተጨዋቾች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳላካቸው ገለጸ

በዓመታዊው የጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ ለመካፈል ወደ ስዊድን ያመሩ ታዳጊዎች እና የቡድን አባላት በስዊድን መጥፋታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ዙርያ ምላሽ ወይም ማብራርያ በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ «ፌዴሬሽናችን የቡድኑ አባላት መጥፋት ያሳዘነው መሆኑን እየገለጸ ታዳጊ ቡድኖች በመሰል ውድድሮች ላይ በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል ወደ ውድድሩ የሚያመሩ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የወከሉ አለመሆኑን እየገለፅን በአንዳድ አካላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት እንደሆኑ እየተገለጸ ያለው መንገድ ትክክል አለመሆኑን እናሳውቃለን።» ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል
