
ማርካ ኢትዮጵያ ስፖርት ሚዲያ (Marca Ethiopia Sport Media) በሀገራችን ስፖርት በተለይም በአትሌቲክስ ዘርፍ ላይ ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለስፖርት አፍቃሪው ተደራሽ ለማድረግ የሚሠራ የጋዜጠኝነት ተቋም ነው።
በቅርቡ በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በተካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ስምንት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሳይጓዙ መቅረታቸውን አስመልክቶ የዓለም አትሌቲክስ (World Athletics) ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል። በዚሁ መግለጫው ላይ ጉዳዩን በተመለከተ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ከራሱ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀጥታ በተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ብቻ ተመስርተው ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
መሉውን መግለጫ ያንብቡ!

ሰላም ወሰንስገድ፣
እባክዎን ከዚህ በታች የዓለም አትሌቲክስ መግለጫ ይመልከቱ፡
የዓለም አትሌቲክስ አትሌቶችን ሚስጥራዊነት በጣም በቁም ነገር ስለሚመለከት ስለግለሰብ አትሌቶች አስተያየት አይሰጥም። አትሌቶች ወደ ውድድሮች አለመሄዳቸው የተለመደ አይደለም፣ በተለያዩ ምክንያቶች።
እንደ ቡድን፣ ስምንት ኢትዮጵያዊ አትሌቶች በዩጂን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ አልተጓዙም። ግለሰቦች እና ሚዲያዎች ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ወይም ከማንኛውም አትሌት በቀጥታ በተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ብቻ ሪፖርት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
ሲል ገልጿል፤በሌላ በኩል ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትናትና ይህንኑ በመንተራስ ጥያቄዎችን በኢሜል ለፌዴሬሽኑ 1. በሆርሞን ምርመራ ምክንያት ስለቀረችው አትሌት
- ስላልተጓዙት ቀሪዎቹ አትሌቶች
- የወደፊት መፍትሄዎች እና ተጠያቂነት
ስለሚሉትና ስሌሎችም ጉዳዮች ጥያቄውኦችን አቅርበን የፌዴሬሽኑን ምላሽ እየተጠባበቅን ሲሆን ፌዴሬሽኑ ምላሹን እንደሰጠን ወደ እናንተ መልሰን የምናቀርበው ይሆናል!
