ኢትዮጵያ የ2026 የዓለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲቫልን ለመጀመሪያ ጊዜ ታዘጋጃለች።

0
IMG_20261101_104843_034

የኢትዮጵያ ዳማ አሶሴሽን በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከህዳር 24 እስከ ታህሳስ 26/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደውን የ2026 የአለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲቫል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አስመልክቶ ዛሬ በወጣቶችና ሰፖርትሚኒስቴር ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ፡፡

ከ40 ሀገራት የተወጣጡ 80 ሰፖርተኞችን በሚያሳትፈዉ የአለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲባልን ሀገራችን ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ መመረጧ በስፖርት ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያ በከናወነችው መጠነ ሰፊ መሰረተ ልማት የአህጉር አቀፍ እናአለም አቀፍ የስፖርት ሁነቶች ማአከል እየሆነች መምጣቷን ማሳያ እንደሆነ የወጣቶችና ሰፖርት ሚኒስቴር የሰፖርት ልማትዘርፍ መሪ ስራ አሰፈፃሚ አበባ አማረ (ዶ.ር ) ተናግረዋል ፡፡

በማከልም አበባ አማረ (ዶ.ር ) መንግስት ለስፖርት ልማት ዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ በሰራቸው ስራዎች የሰው ዘር መገኛ የሆነችውን ሀገራችን በስፖርት ዲፕሎማሲና በሰፖርት ቱሪዝም ለአለም በማስተዋወቅ ሰፖርት ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ፋይዳ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንዲቻል እያስቻለ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ዳማ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኦማር ታየር በበኩላቸው የዳማ ሰፖርት በአህጉራችን ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዮኒቨርሲቲ ድረስ ባሉ የትምህርት ማአከላት የሚዘወተር የሰው ልጅ የእምሮውን የማንሰላሰል አቅሙን፣ ምክኒያታዊነቱን እና የውሳኔ ብቃቱን የሚተገብርበት ተወዳጅ ስፖርት መሆኑን በመግለፅ ኢትዮጵያም በላት መሰረተ ልማት ከአፍሪካ ሀገሮች በመመረጥ ፌስቲቫሉን አዘጋጅ መሆኗ ለስፓርቱ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዳማ አሶሴሽን ከ14 አመታት ትጋት በኋላ በሃገራችን የስፖርት ልማት ዘርፍ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ውድድሩን ለማዘጋጀት እድሉን ማግኘቱ የዳማ ስፖርትን በመላ ኢትዮጵያ ለማስፋፋትና ተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት የሚያስችል ነው ያሉት የአዲስ አበባ ዳማ አሶሴሽን ፕሬዘዳንት አቶ ታድሎ ደሳለኝ ናቸው።

ዳማ ለወጣቶች፣ ለዕውቀት፣ ለወዳጅነት እና ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ከህዳር 24/2019 ዓ.ም አስከ ታኅሣሥ 06/2019 ዓ/ም የሚካሄደው የ2026 የአለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ግራንድ ኤሊያና ሆቴል እና አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ተገልፆል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail