
ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በአለም ላይ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 8’ ውድድርን ሁለተኛ በመሆን በማጠናቀቅ ዳግመኛ ታሪክ ሠርቷል።
ኤርትራዊው አትሌት ቢኒያም ግርማይ በቱር ደ ፍራንስ (Tour de France) የብስክሌት ውድድር ዛሬ በተካሄደው 8ኛ ውድድር 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል。
ቢኒያም (የ NSN ሳይክል ቡድን አባል) ሲሆን በፈጣኑ የፍጻሜ ፉክክር ቤልጅየማዊውን አሸናፊ ቲም ሜርሊየርን (Tim Merlier) ተከትሎ ሁለተኛ በመሆን በመግባት ውድድሩን አጠናቋል。
የቱር ደ ፍራንስ 2026 – ተዋቂው ብስኪለተኛ ሜርሊየር በበርጌራክ የደረጃ ስምንት ውድድርን በአንደኝነት በማሸነፍ ውድድሩን አጠናቋል

ኤርትራዊው ቢንያም በ 2022 በዢሮ ዲኢታሊያ የመጀመሪያውን ትልቅ ‘ስቴጅ’ በማሸነፍ በብስክሌት ውድድር ያለውን ስም ከፍ ማድረግ ችሎ ነበር።
«ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን እላለሁ» ሲል ቢንያም ተናግሯል።
«ብስክሌት መንዳት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር ላይ እወዳደራለሁ የሚል ህልም አልነበረኝም። አሁን የሆነውን ግን ማመን አልቻልኩም። ቤተሰቦቼን፣ ባለቤቴን፣ ኤርትራን እና አፍሪካን አመሰግናለሁ» ብሏል።
«መኩራት አለብን። አሁን በትልልቅ መድረኮች ከመሳተፍ ባለፈ ስኬትም አስመዝግበናል። አሁን የእኛ ጊዜ ነው፣ ይህ የእኛ ጊዜ ነው። ይህ ለመላው አፍሪካ ነው»ሲል «የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ» ተብሎ የሚታወቀው ቢንያም ተናግሮ ነበር።
