የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የቦክስ ማህበር (World Boxing) አባል ሆነች🥊🇪🇹

0
Screenshot_2026_0811_092722~2

ዓለምአቀፉ የቦክስ ማህበር ባወጣው መረጃ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ5 አገራትን የአባልነት ጥያቄ ማፅደቁን አሳውቋል።

ይህንኑ አስመልክቶ አቶ እያሱ መሰን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ “World Boxing”ን በመቀላቀሏ የተሰማኝን ጥልቅ ደስታ እየገለፅኩ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ። ይህ ለኢትዮጵያ የኩራት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አንድ የአፍሪካ የቦክስ ቤተሰብ ለሁላችንም የደስታና የክብር ወቅት ነው ብለዋል።

አክለውም በአህጉራችን ስፖርታችንን የሚያጠናክር እያንዳንዱ እርምጃ ለሁላችንም ድል ነው። ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ ይህ አዲስ ምዕራፍ ለአፍሪካ ቦክስ ታላላቅ እድሎችንና ስኬቶችን ያመጣ ዘንድ እመኛለሁ ሲሉ ደስታቸውን ገልፀዋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail