
በኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ለሁሉም ክፍት የሆነ የክለቦች ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የክለቦች ሻምፒዮና እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተጠናቋል።
ፌዴሬሽኑ ባካሄደው ሻምፒዮና እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ ከክልልና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ክለቦች እና ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።
ፌዴሬሽኑ ከክለቦች ሻምፒዮና ጎን ለጎን በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን ለተከታታይ ቀናት ሰጥቷል።
አቶ እያሱ ወሰን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ።

የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀርሞኒ ሆቴል አካሂዷል።
መደበኛ ጉባኤው አቶ እያሱ ወሰንን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ያለፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በማፅደቅ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መክሯል።
መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በበጀት ዓመቱ እቅድ አፈፃፀም፣ በተሻሻለው የፋይናንስ መመሪያ፣ እንዲሁም የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈፃሚ ምርጫ በአጀንዳነት ይዞ ከመከረባቸው አጀንዳዎች መካከል ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የቦክስ ማህበር (World Boxing) አባል ሆነች🥊🇪🇹

ዓለምአቀፉ የቦክስ ማህበር ባወጣው መረጃ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ5 አገራትን የአባልነት ጥያቄ ማፅደቁን አሳውቋል።
ይህንኑ አስመልክቶ አቶ እያሱ መሰን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ሳቦም አበራ ሚልኬሳን በፕሬዚዳንትነት መረጠ ።

የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። ጉባኤው የኦዲትና የስራ ሪፖርቶችን መርምሮ በማጽደቅ፣ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያቶ በማፅደቅ እና አዳዲስ የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሳቦም አበራ ሚልኬሳ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ፌዴሬሸኑ ባላፉት ዓመታት የቴኳንዶ ስፖርትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ በማድረግ በዘረጋው የውድድር መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮናዎችን፣ የግል እና የቡድን ውድድሮችን በዕድሜና ክብደት ደረጃ በማካሄድ ዉጤታማ ስራዎችን እንደሰራ አውሰተዋል።
የአፍሪካ ቼስ ኮንፌዴሬሽን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤን በአዲስ አበባ ከተማ አካሄደ

የአፍሪካ ቼስ ኮንፌዴሬሽን ሁሉም አባል ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።
ሁለት አጀንዳዎች ላይ በትኩረት መክሮ የቀጣይ አራት ዓመታት መሪውን የመረጠው የአፍሪካ ቼስ ኮንፌዴሬሽን ጉባዔ የ2025/26 የአፈፃፀም ሪፖርቱን እና የፋይናንስ ሪፖርቱን ለጉባዔተኛው ለውይይት አቅርቦ አስተያየት በማሰጠት አፅድቋል።
አቶ ቢኒያም ነገሱ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።
ለኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት ድሬዳዋን በመወከል በእጩነት የቀረቡት አቶ ቢኒያም ነገሱ በ14 ድምፅ አሸናፊ ሆነዋል።
