Athletics

በስዊዘርላንድ ዙሪክ በተካሄደው የዌልትክላሴ (Weltklasse Zürich) ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ሁለት አዳዲስ የዓለም ክብረ ወሰኖች ተሰበሩ

ትናንት ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም (August 27, 2026) በስዊዘርላንድ ዙሪክ በተካሄደው የዌልትክላሴ (Weltklasse Zürich) ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ሁለት አዳዲስ የዓለም ክብረ ወሰኖች የተሰበሩበት እና እጅግ አስደናቂ ውጤቶች የተመዘገቡበት ታሪካዊ ምሽት ነበር።

የስዊዘርላንድ የዌልትክላሴ ዙሪክ (Weltklasse Zürich) ዳይመንድ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ነው

የስዊዘርላንድ የዌልትክላሴ ዙሪክ (Weltklasse Zürich) ዳይመንድ ሊግ ውድድር ከኦገስት 26 እስከ 27 ቀን 2026 ዓ.ም በዙሪክ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ታዋቂ የአትሌቲክስ ውድድር የዳይመንድ ሊግ የነጥብ ማሰባሰቢያ የመጨረሻው መደበኛ ውድድር (የ14ኛው ምዕራፍ) ነው።

ደማቅ አቀባበል ለጀግኖች አትሌቶች ዮሚፍ እና ፎቴን!

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበው ጀግናው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሴቶች የውድድሩን አዲስ የቦታ ክብረወሰን በማስመዝገብ ያሸነፈችው ጀግናዋ አትሌት ፎቴን ተስፋይ ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጁ

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል ።

በሰሜን አየርላንድ ላርን ከተማ በተካሄደው Antrim Coast Road Race ውድድር፣ በዚህ ዓመት አዲስ በተጨመረው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን የበላይነታቸውን አሳይተዋል።

ፎቴን ተስፋይ የ2026 ቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶንን አሸነፈች

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የ2026 የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት ፎቴን ተስፋይ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ 21 ኪሎ ሜትሩን 1:03:57 በሆነ ጊዜ በመጨረስ የውድድሩን የቦታ ክብረ ወሰን በማሻሻል በአንደኝነት አሸንፋለች ።

ዮሚፍ ቀጄልቻ በግማሽ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበ

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከደቂቃዎች በፊት በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

አትሌቱ 21 ኪሎ ሜትሩን 56:51 በሆነ ጊዜ በመጨረስ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።

በዚህም በዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ የነበረውን 57:20 የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል አዲሱን የዓለም ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።

አሜሪካ የተጓዘው የልዑካን ቡድን ተመለሰ፤አሜሪካ ሀገር ስለጠፉ 4 የኢትዮጵያ አትሌቶች እና 3 አሰልጣኞች ምን አዲስ ነገር አለ?

በአሜሪካ በተካሄደ የውድድር ልዑካን ቡድን ውስጥ የነበሩ 4 የኢትዮጵያ አትሌቶች እና 3 አሰልጣኞች (በድምሩ 7 ሰዎች) ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ እዚያው መቅረታቸው (መኮብለላቸው) ታውቋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አባላት የነበሩት እነዚህ ግለሰቦች፣ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ በሚመለሰው የበረራ መስመር ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል። የቡድኑ አባላት ከአሰልጣኞቻቸው ተለይተው የቀሩት ፖርትላንድ (ኦሪገን) ከተማ ላይ እንደሆነ ይፋ ሆኗል።

የዓለም አትሌቲክስ (World Athletics) ይፋዊ መግለጫ በዝግጅት ክፍላችን በኩል አስተላለፈ

ማርካ ኢትዮጵያ ስፖርት ሚዲያ (Marca Ethiopia Sport Media) በሀገራችን ስፖርት በተለይም በአትሌቲክስ ዘርፍ ላይ ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለስፖርት አፍቃሪው ተደራሽ ለማድረግ የሚሠራ የጋዜጠኝነት ተቋም ነው።

ለኮፐንሃገኑ የዓለም ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌቶች ተመረጡ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳሳወቀው በመጪው መስከረም ወር ለሚካሄደው የዓለም የግማሽ ማራቶን አትሌቲስ ሻምፕዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፤

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3 ኛ ሆና አጠናቀቀች

በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን በተካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማጠቃለያ ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች እጅግ አስደናቂ ታሪክ በመስራት በድምሩ 2 ወርቅ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ (በድምሩ 6 ሜዳሊያዎችን) በመሰብሰብ በዓለም 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ወጣት አትሌቶቻችን በአሜሪካ ኦሪገኑ ውድድር ድልን እየተቀዳጁ ነው ፤ውድድሩ ዛሬ ያበቃል

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት በተካሄዱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ያስመዘገባቸው ታላላቅ ውጤቶች በሁለት ዋና ዋና ሻምፒዮናዎች ይከፈላሉ። አንደኛው በ2022 የተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና (ታላላቆች) ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በአሁኑ ወቅት (ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም./ኦገስት 2026) እየተካሄደ ያለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው።

የሁለቱም ውድድሮች ይፋዊ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ እና የወርቅ አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦

የኦሪገን 2022 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና (የአዋቂዎች) ውጤት

ኢትዮጵያ በዚህ ታሪካዊ ውድድር ላይ 4 ወርቅ፣ 4 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአሜሪካ በመቀጠል በዓለም 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ሜዳሊያየአትሌት ስምየውድድር ዓይነት

የኦሪገን 2026 የዓለም ከ20 ዓመት በታች (U20) አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤት

የአሜሪካን የኦሪጋኑ ውድድርና የፌስቡኩ ውዥንብር!

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሃይዋርድ ፊልድ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች።

ውድድሩን በተመለከተ እስካሁን የተመዘገቡ ውጤቶች

አትሌት አልማዝ ዮሃንስ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል በ9፡15.81 አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፣ አትሌት ወሰኔ አሰፋ በ9፡30.50 ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

አትሌት ሽቶ ጉሚ በ5ሺህ ሜትር በ15፡07.21 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ አስመዝግባለች።

አትሌት ዳምጠው ከበደ በ5 ሺህ  በ13፡35 ሶስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

አጠቃላይ ኢትዮጵያ እስካሁን በውድድሩ 1 የወርቅ፣ 2 የብር እና 1 የነሀስ (በድምሩ 4) ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች።

የሰሞኑ የፌስቡክ አነጋጋሪው

አጃይባ አልዬ ከውድድር መቅረት፦ በቅርቡ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ400 ሜትር ታሪካዊ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችውና በዚህ ውድድር ትልቅ ተስፋ የተጣለባት አትሌት አጃይባ አልዬ፣ ከዓለም አትሌቲክስ ውድድር በደረሳት የሆርሞን (ቴስቶስትሮን)  ውጤት  ውጪ መሆኗ ስፖርተኛውንና ደጋፊዎቿን እያነጋገረ ይገኛል።


ሰሙኑን በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል ።

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ ድል እና አዲስ የግል ምርጥ ሰዓቶች አስመዝግቧል

በዓለም አቀፍ ደረጃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 10ኛው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ በአስደናቂ ፉክክር፣ በአዳዲስ የዓለምና የውድድር ክብረወሰኖች መሻሻል እንዲሁም በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ ውጤት ታጅቦ ተጠናቋል።

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

የኢትዮጵያ አትሌቶች በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ፣ በዛግሬብ እና በጋቦን የጎዳና ላይ ውድድሮች ደማቅ ድሎችን አስመዘገቡ

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር በማድረግ አበረታችና ደማቅ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።

የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ 7ኛ ምዕራፍ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ሲከናወን፣ አትሌቶቻችን የግላቸውን እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች በማሻሻል አንጸባርቀዋል።

ፈጣን ፉክክር በተስተዋለበት የሴቶች 1,500 ሜትር ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፣አትሌት ፍረወይኒ ኃይሉ የዓመቱን ምርጥ ብቃቷን አሳይታለች።
አትሌት ፍረወይኒ የዓመቱን የራሷን ፈጣን ሰዓት 3:55.92 በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

በእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያዊው ምስጋና ዋኩማ በብራዚል ውድድር በማሸነፍ ታሪክ መዝገብ ውስጥ ገባ

በእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያዊው ምስጋና ዋኩማ በብራዚል ውድድር በማሸነፍ ታሪክ መዝገብ ውስጥ ገባ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የእሽቅድምድም ላይ ተካፋይ የሆነው ምስጋና ዋኩማ በአስደናቂ ሁኔታ የግማሽ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸንፊ ሆነ።

 

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ