
የኢትዮጵያ ስፖርት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ መሆነ ካልቀረ መቼም የሀገሪቱ ስፖርት አያድግም

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለው የመጀመርያው የፊፋ ከ15 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫና ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (የወደፊቱ ዋሊያዎች) የገጠማቸው ተከታታይ ሽንፈት ለብዙ የስፖርት አፍቃሪዎች እጅግ አሳዛኝ እና አሳሳቢ ክስተት ነው። ቡድኑ በምድብ 8 (Group H) ውስጥ ባደረጋቸው ጨዋታዎች በሶሪያ 2 ለ 0፣ በሀንጋሪ 3 ለ 0 እና በማሌዥያ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት መሸነፉ የታዳጊዎች እግር ኳስ አያያዛችንን በትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር የችሎታ ወይም የፍቅር ማጣት ሳይሆን የአመራር እና የስርአት ብልሽት ነው

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ማህበራዊ ሃያሲ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በሴካፍ (CECAFA) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በዩጋንዳ አቻው 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉ የስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ድንጋጤና ቁጭትን መፍጠሩ ይታወሣል ።ለዚህ ሽንፈት ተጠያቂዎቹ ተጨዋቾቹና አሰልጣኞቹ ሣይሆኑ በሀገሪቱ እግር ኳስ ላይ ያለው መዋቅራዊ ችግር ነው፤«በሀገሪቱ እግር ኳስ ላይ ያለው መዋቅራዊ ችግር» ስንል ችግሩ የአንድ ጨዋታ፣ የአንድ አሰልጣኝ ወይም የአንድ ትውልድ ተጫዋቾች ድክመት ብቻ ሳይሆን፤ አጠቃላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሚመራበት ሥርዓት (System) ካለበት መሰረታዊ እክሎች የመነጨ ነው ማለት ነው።በዚህ ዙሪያ ለዛሬ የምለው ይኖራል።
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የለተመልካች ተጀምሯል፤የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወቅታዊ ፈተናዎች

(ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ )
ዓርብ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም (October 9, 2026) የተጀመረው የ2019/2027 የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታዎች በጠንካራ ፉክክርና ያልተጠበቁ ውጤቶች የታዩበት ሆኖ ጅማሮ ሆኗል።
የአዳማ ከተማ አስገራሚ ድል
አዳማ ከተማ ወደ ሊጉ የተመለሰውን ኢትዮ ኤሌክትሪክን (መብራት ኃይል) 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ፣ ከ2013 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን መክፈቻ ጨዋታ በድል መጀመር ችሏል።
የአዲስ አደጎቹና የነባሮቹ አቻ መለያየት
ወደ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደገው ሀላባ ከተማ በሜዳው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አስተናግዶ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የተደረጉት ሁለቱም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በጠንካራ ፉክክር ያለ አሸናፊ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
አዲሱ ሚኒስትር ፖለቲከኞች ሳይሆን የስፖርት ባለሙያተኞች በዙሪያቸው ማደራጀት አለባቸው
ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)

በቅርቡ በተደረገው የአስፈጻሚ አካላት አዲስ አወቃቀር መሠረት የኢትዮጵያ ስፖርት ዘርፍ የአደረጃጀት ለውጥ ተደርጎበታል።
ቀድሞ የነበረው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተከፋፍሎ፣ ስፖርቱ ከወጣቶች ጉዳይ ጋር በመገናኘት የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ተብሎ እንደ አዲስ ተዋቅሯል። ይህንን ሚኒስቴር እንዲመሩ ዶ/ር አክሊሉ ታደሰ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ከስፖርት የተለየው የባህል ዘርፍ ደግሞ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመቀላቀል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚል ተዋቅሯል። ይህንን ዘርፍ ደግሞ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርነት እየመሩት ይገኛሉ።
የቀድሞ የስፖርት ፖሊሲ ድክመቶች እና ለስፖርቱ መሞት ያላቸው ድርሻ

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
ከ25 አመታት ወጥቶ የነበረውና ላለፉት አያሌ ዓመታት በሥራ ላይ የነበረው በወያኔ ጊዜ ወጥቶ የነበረው የስፖርት ፖሊሲ ለዛሬው ውድቀት ትልቅ መሠረት ጥሏል። ፖሊሲው የሚከተሉት ዋና ዋና ስብራቶች ነበሩት።
ስፖርቱ በሙያዊ ባለሙያዎች ሳይሆን በፖለቲካ ታማኝነትና በክልላዊ ውክልናዎች እንዲመራ መንገድ ከፍቷል。 ፌዴሬሽኖች የባለሙያ መፈልፈያ ሳይሆኑ የፖለቲከኞች መደበቂያ ሆነው ቆይተዋል።
የድሮው ፖሊሲ ስፖርትን ከትምህርት ሥርዓቱ (School Curriculum) ጋር ማስተሳሰር ባለመቻሉ በትምህርት ቤቶች ይደረጉ የነበሩ የውድድር መድረኮች ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ አድርጓል። ይህ ደግሞ እንደ እጅ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ መረብ ኳስ እና ጠረጴዛ ቴኒስ ያሉ ሌሎች ስፖርቶች በሀገሪቱ ውስጥ ጨርሰው እንዲሞቱ አድርጓል።
ችግሩ ወንበሩ ሳይሆን ቡድኑ ነው መፈተሽ ያለበት

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
ይህን ርዕስ መርጬ ለመጫጫር የፈለኩት ያለምክንያት አይደለም ፤በአብዛኛው የስፖርት ሚዲያ ተዋቂ የተባሉ ጋዜጠኞች ጭምር እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአሰልጣኝ የዮሐንስ ሳህሌ ከሴኔጋል ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በነበረው ጨዋታ ላይ ከመቀመጫቸው ያለመነሳታቸው ጉዳይ በሰፊው አሁን ድረስ እየተወራ መሆኑ ነው፤ስለ ውጭ የስፖርት ወሬ የሚተነትኑልን ተዋቂ ጋዜጠኞቻችን ለዚህ ወሬ ቦታ መስጣታቸው እራሱ ገርሞኛል፤ለምን ብትሉኝ በርካታ አንቱ የተባሉ አሰልጣኞች ከወንበራቸው መነሳት የማይፈልጉ እንዳሉ ስለማውቅ፤የውጭ ጨዋታዎችን ሲያስተላልፉልንና ሲያወሩልን ይህን እንዴት አለማስተዋላቸው ገርሞኝ ነው።እንደ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሙሉ 90 ደቂቃ ብቻ ሳይሆን እድሜ ልካቸውን ከመቀመጫ ባለመነሳት የማታወቁ ተዋቂ የዓለማችን ውጤታማ አስልጣኞች እንዳሉ እርሶስ ያውቃሉ? በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ “ከመቀመጫቸው ስለማይነሱ”ሷሰልጣኞች በተመለከተ በሁለት የተለያየ ትርጉም ሰጥተን ማየት እንችላለን ።ከወንበራቸው ሳይነሱ ጨዋታንውን እያዩ በሞት ያጣናቸው አሉ፤ ይህ ማለት የሚያሰለጥኑትን ቡድን እየመሩ ወንበራቸው ላይ እያሉ ሕይወታቸውን የጨረሱ ታዋቂ አሰልጣኞች አሉ። በሌላ በኩል 90 ውም ይሁን ተጨማሪው ደቂቃ እስከሚያልቅ ከወንበራቸው የማይነሱ አሰልጣኞች ነበሩ አሁንም አሉ።
አሰልጣኞችን ማብጠልጠሉ ጥቅም የለውም ፤መሥራትና እኔ ማን ነኝ ብሎ እራስን መፈተሽ ያስፈልጋል

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናትና በሴኔጋል 1ለ0 ተሸንፎ መውጣቱ ይታወሣል፡፡አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በወቅቱ “አንድም ጊዜ ከመቀመጫው ሳይነሳ ጨዋታውን ጨረሰ” የሚለውን የአብዛኛውን ሚዲያ ትችት በበኩሌ አልስማማበትም፤ ይህ የአሰልጣኙን የስራ ባህሪ እና ታሪክ ሙሉ በሙሉ የሚያንፀባርቅ አይደለም።
ይህንን አስተያየት በተመለከተ የእግር ኳስ ባለሙያዎች እና ደጋፊዎች የሚሰነዝሯቸውን ሁለት የተለያዩ እይታዎች በገለልተኝነት ማየት እንችላለን ።
ሚዲያው የህዝብ ጠባቂ (Watchdog) መሆኑ ቀርቶ የንግድ ድርጅቶች ማርኬቲንግ መሳሪያ ሆነዋል

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
በከፍተኛ ጉጉት ተጠብቆ የነበረው ኢትዮ ፋይት ናይት (Ethio Fight Night) ዝግጅት፣ ከከፍተኛ የቲኬት ዋጋ መናር ጋር በተያያዘ እና ዋናዎቹ ፍልሚያዎች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በመጠናቀቃቸው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቅሬታና ትችት አስተናግዷል። መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም (September 19, 2026) በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል (AICC) የተካሄደው ይህ የኤምኤምኤ (MMA) እና የኪክቦክሲንግ ፍልሚያ ምሽት በርካታ ተመልካቾችን ቅር አሰኝቷል።
ክለቦችም ሆኑ የክልል ፌዴሬሽኖች ራሳቸው በጥቅምና በሙስና መዋቅር የተሳሰሩ ከሆኑ

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
የሀገሪቱን እግር ኳስ እድገት በዘላቂነት ለማምጣት የአስተዳደር እና መዋቅራዊ ለውጥ መኖር ወሳኝ መሆኑ በብዙ የስፖርት ባለሙያዎችና ደጋፊዎች ዘንድ በሰፊው የሚደገፍ ሃሳብ ነው። በአንጻሩ፣ በሜዳ ላይ የሚታዩ ስልቶች (ታክቲክ) እና የተጫዋቾች ምርጫም የራሳቸው የፈጣን ውጤት ተፅዕኖ እንዳላቸው የሚከራከሩ አሉ።
በዓለም ላይ እግር ኳሱ የተያዘው በስፖርቱ አፍቃሪዎች ሳይሆን፣ በስልጣን፣ በገንዘብ እና በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ በተሳሰሩ የአጭበርባሪዎች ስብስብ ነው

ከወሰንሰገድ መርሻ ድምሴ
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
ትችታችንን መጀመሪያ ከደካማው ሴካፋ ተነስተን መዳረሻችንን ፊፋ ላይ እናደርጋለን፡፡ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ በታንዛኒያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ20 አመት በታች ውድድር ነው፡፡ የሴካፋ (CECAFA) ውድድሮች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ እና አሁን ላይ የሚገኙበት ደረጃ በብዙ ስፖርት አፍቃሪዎችና ባለሙያዎች ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያና የትችት መድረክ መሆኑ እውን ነው። ውድድሩን “ደካማ” የሚያሰኙት በርካታ ተጨባጭ ምክንያቶችና ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለቀጠናው እግር ኳስ እድገት የሚሰጠው የራሱ የሆነ ፋይዳ አለው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲሱ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፌዴሬሽኑን ከሙስና የጸዳ እንዲሆን በማድረጉ በኩል ጠንካራ ስር ነቀል የማፅዳት ሥራ ይጠብቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናትና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ተካሄዶ አቶ ኢሳያስ ጅራ ከአጠቃላይ 99 መራጭ 81 ድምፅ በማግኘት ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል። ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ፣ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ ወ/ሮ ሰርካለም ሳሙኤል፣ ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉሥ፣ አቶ አበባው ሰሎሞን፣ አቶ አንበሴ አበበ እና አቶ ደመላሽ ይትባረክ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።
የኢትዮጵያ ስፖርት ችግር የተሰጥኦ (Talent) እጥረት ሳይሆን የአመራር፣ የስርዓት እና የእይታ (Vision) እጥረት ነው

የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ሌላውን ትተን በተለይም እግር ኳስ እና አትሌቲክስ በተለያዩ የፖለቲካ እና የሥርዓት ለውጦች ውስጥ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፈዋል ። በደርግ ዘመን የነበረው የስፖርት መዋቅር፣ በኢህአዴግ (ወያኔ) ዘመን የታዩት ለውጦች እና አሁን ያለው ወቅታዊ ደካማ አፈጻጸም በስፖርት ባለሙያዎችና አፍቃሪያን ዘንድ ሰፊ ክርክር የሚደረግባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
የኢትዮጵያ ስፖርት ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የደከመበትንና ካለፈው የስፖርት እንቅስቃሴ አንጻር ወደ ኋላ የቀረበትን ምክንያቶች እንመልከት።
መንግሥት አለአግባብ እየባከነ ያለውን ለስፖርቱ ዘርፍ የሚመድበውን የገንዘብ መጠን ማቆም አለበት

(ከወሰንሰገድ ምርሻ ደምሴ)
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ)
መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ የሚመድበው የገንዘብ መጠን በተለያዩ የመንግሥት እርከኖች (በፌደራል፣ በክልል እና በከተማ መስተዳድሮች) ተከፋፍሎ የሚወጣ በመሆኑ አጠቃላይ ድምሩን በአንድ ማዕቀፍ ማስቀመጥ ባንችልም ከፍተኛ ገንዘብ ይመድባል ። ነገር ግን የሀገሪቱን የፋይናንስ መረጃዎች እና አጠቃላይ መዋቅሩን መነሻ በማድረግ ወጪው በሶስት ዋና ዋና መንገዶች ለስፖርቱ ብሎ እንደሚያፈስ መረዳት እንችላለን ።
ውጥንቅጡ የወጣውን የኢትዮጵያን ስፖርት እንዴት ወደ ከፍተው ማማ እንመልሰው ?

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ )
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ብቸኛ ዕጩ ተወዳዳሪ በሆኑት በአቶ ኢሳያስ ጅራ የቀረቡትን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ተጠባባቂዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበረሰብ እና በስፖርት ተንታኞች ዘንድ የተለያዩ እይታዎችንና አስተያየቶችን እያስነሳ ይገኛል።
ይህን አዲስ አሰራር እና የቀረበውን ዝርዝር በተመለከተ በሁለት መልኩ ሊጠቃለሉ ይችላሉ
- አዎንታዊ እና ደጋፊ እይታዎች (የባለሙያ ስብጥር እና ብቃት)
